ፊልጵስዩስ 1፡ ወንጌልን መስበክ
ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ መልእክቱ እንደ ሁልጊዜው በሰላምታ ይጀምርና ወደ ምስጋናና ጸሎት ያልፋል።
"ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ እናንተ ሁሉ በደስታ እየጸለይሁ፥ ከፊተኛው ቀን እስከ ዛሬ ድረስ ወንጌልን በመስበክ አብራችሁ ስለ ሠራችሁ፥... በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤ በእስራቴም ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ በማድረግ ሁላችሁ ከእኔ ጋር በጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ" (ፊልጵስዩስ 1፥3_7)
📌 የፊልጵስዩስ ቤተክርስቲያን አሁን ላለነው አብያተ ክርስቲያናት ምሳሌ የምትሆን ናት። መልእክቱን ሲጽፍ እንደ ቤተክርስቲያን ነው የሚጽፈው። ምክንያቱም ወንጌልን የሚሰብኩት እንደ ቤተክርስቲያን ነውና። ወንጌልን መስበክ ለአገልጋይ የተዉት ነገር አልነበረም።
የተፈጠሩለትን መልካም ስራ እያደረጉት እየኖሩለት ነበር። ይህ መልካም ስራ ደግሞ እስከ ክርስቶስ ቀን ድረስ የሚቀጥል ነው። ይህ መልካም ስራ በምድር ያለንበት ዋናው ምክንያት ነ።
“እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።” (ኤፌሶን 2፥10)
📌 ሐዋርያው ጳውሎስ አንድ ነገር ሁሌም ይጸልይላቸዋል። እርሱም ፍቅራቸው በእውቀት እና በማስተዋል እያደገ እንዲበዛ፤ የፍቅራቸው ማደግ የሚያስከትለው ውጤት አለ። እርሱም የሚሻለውን ፈትኖ መውደድ፣ የጽድቅ ፍሬ ማፍራት እና ምስጋናን መሞላት ናቸው።
እነዚህ ውጤቶች የመንፈሳዊ እድገት መገለጫ ናቸው፤ መሰረታቸውም ፍቅር ነው። መንፈሳዊ ዕድገት እና የአገልግሎት ዕድገት የምንላቸው ፍቅር ላይ ካልተመሰረቱ እድገት አይደሉም፤ ቢመስሉም አይደሉም!!
"ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።" (1ኛ ቆሮንቶስ 13፥2_3)
ፍቅራቸው እዴት ይብዛ? በእውቀት እና በማስተዋል።
እውቀቱም በእግዚአብሔር የተወደዱበት ፍቅር እውቀት ነው፤ እንደተወደዱት እንዲወዱ፥ ስለተወደዱ እንዲያመሰግኑ ነው።
"እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።" (ኤፌሶን 5፥1_2ኤፌሶን 5፥1_2)
ጌታብቻ ተስፋዬ እንደጻፈው
ለሌሎች አካፍሉልን!
@gracecom

Comments