ክርስቶስ ብቻ (Christ Alone)

 ክርስቶስ ብቻ (Christ Alone)




ሞኖርጊዝም - የአንዱ ሥራ

ሲንጋርጊዝም - የብዙዎች ጥምር ጥረት

"ክርስቶስ ብቻ" የሚለው ቃል በመቤዠት ውስጥ የክርስቶስ የበላይነት እና የብቃት አዋጅ ነው፡፡

ቤዛነት ለሁሉም የመንፈሳዊ መገለጥ መሠረት ነው። ቤዛነትን መረዳት ማለት ደግሞ የእግዚአብሔርን ልብ ማየት ነው።

1. ክርስቶስ ብቻ ወልድ ነው

1.1 ክርስቶስ ከምድራዊ ልደቱ በፊት የዘላለም አምላክ ነው። 

"እርሱ የማይታየው አምላክ አምሳል ነው፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ላይ ተያይዞ የጸናው በእርሱ ነው። እርሱ አካሉ የሆነችው የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ በሁሉ ነገር የበላይነት ይኖረው ዘንድ እርሱ የመጀመሪያ፣ ከሙታን መካከልም በኵር ነው። እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በእርሱ ይሆን ዘንድ ወዶአልና፤" (ቈላስይስ 1:15-19) NASV)

1.2 ክርስቶስ በምድራዊ ሕይወቱ አምላክ ነው። 

"የመለኮት ሙላት ሁሉ በአካል በእርሱ ይኖራልና፤" (ቈላስይስ 2:9 NASV)

1.3. ክርስቶስ ከትንሣኤው በኋላ አምላክ ነው። 

"እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ፤" (ቈላስይስ 3:1 NASV)

2. ክርስቶስ ብቻ አዳኝ ነው

"እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤" (ቈላስይስ 1:13 NASV)

"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤" (ዮሐንስ 3:16 NASV)

2.1 በጨለማው አገዛዝ ስር ነበርን። 

"እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤" (ቈላስይስ 1:13 NASV)

2.2 ከእግዚአብሔር የተለየን እና ጠላቶች ነበርን። 

"ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በአሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ።" (ቈላስይስ 1:21 NASV)

2.3 መላ ሰውነታችን በኃጢአታዊ ባሕሪ ይገዛ ነበር። 

"በእርሱ ሆናችሁ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ ተገረዛችሁ፤ በክርስቶስም መገረዝ የሥጋን ኀጢአታዊ ባሕርይ አስወገዳችሁ፤" (ቈላስይስ 2:11 NASV)

2.4 በኃጢአታችን ውስጥ የሞትን ነበረን።
 
"እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለ መገረዝ ሙታን ሳላችሁ፣ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አደረጋችሁ ፤ ኀጢአታችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤" (ቈላስይስ 2:13 NASV)

2.5 እኛን በሚቃወመን እና በሚጻረረን የዕዳ ጽዕፈት ውስጥ ነበርን። 

"ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው።" (1 ዮሐንስ 4:10 NASV)

"ሲቃወመንና ሲጻረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰስ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው።" (ቈላስይስ 2:14 NASV)

2.6 በክፉው ኃይሎች እና ባለሥልጣኖች ስር ነበርን። 

"የአለቆችንና የባለ ሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።" (ቈላስይስ 2:15 NASV)

"መልሼ ለማንሣት ሕይወቴን አሳልፌ ስለምሰጥ አባቴ ይወደኛል። ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ አሳልፌ ለመስጠትም ሆነ ለማንሣት ሥልጣን አለኝ፤ ይህን ትእዛዝ የተቀበልሁትም ከአባቴ ነው።" (ዮሐንስ 10:17-18 NASV)



* ትስጉት፦ ክርስቶስ ከእኛ አንድ ሆነ። 

"እግዚአብሔርም ሙላቱ ሁሉ በእርሱ ይሆን ዘንድ ወዶአልና፤ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው ደሙ ሰላምን በማድረግ በምድርም ሆነ በሰማይ ያለውን ነገር ሁሉ በእርሱ በኩል ከራሱ ጋር አስታረቀ።" (ቈላስይስ 1:19-20 NASV)

* ቤዛነት፦  ክርስቶስ የእኛ ምትክ፣ መስዋእት እና ቤዛ ሆነ። 

"እርሱ ከጨለማ አገዛዝ ታደገን፤ ወደሚወደው ልጁ መንግሥትም አሻገረን፤ በእርሱም መዋጀትን በደሙ አግኝተናል፤ ይህም የኀጢአት ይቅርታ ነው።" (ቈላስይስ 1:13-14 NASV)

* ዳግም መወለድ፦ ከክርስቶስ ጋር ሕያው አደረገን። 

"እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለ መገረዝ ሙታን ሳላችሁ፣ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አደረጋችሁ፤ ኀጢአታችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤" (ቈላስይስ 2:13 NASV)

"ኢየሱስም መልሶ፣ እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፣ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ዳግመኛ እንዲወለድ ተመልሶ ወደ እናቱ ማሕፀንስ ሊገባ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ እውነት እልሃለሁ፤ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤" (ዮሐንስ 3:3-5 NASV)

"እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀበል ሁሉ ከቶ አይገባባትም።" (ማርቆስ 10:15 NASV)

* መጽደቅ፦ ክርስቶስ የእኛ ጽድቅ ነው። 

"ሲቃወመንና ሲጻረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰስ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው።" (ቈላስይስ 2:14 NASV)

"አሁን ግን ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤" (ቈላስይስ 1:22 NASV)

"ሕግ በመጠበቅ የሚገኝ የራሴ ጽድቅ ኖሮኝ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን ይኸውም ከእግዚአብሔር የሚመጣ፣ ከእምነትም በሆነ ጽድቅ በእርሱ ዘንድ እንድገኝ ነው።" (ፊልጵስዩስ 3:9 NASV)

* የክብር ልውውጥ፦ ክርስቶስ የእኛን ሥፍራ ወሰደ። 

"እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።" (2 ቆሮንቶስ 5:21 NASV)

* ማስታረቅ፦ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አድርጎናል።

"ከክፉ ባሕርያችሁ የተነሣ ቀድሞ ከእግዚአብሔር የተለያችሁ በአሳባችሁም ጠላቶች ነበራችሁ። አሁን ግን ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ሊያቀርባችሁ፣ በክርስቶስ ሥጋ በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ፤" (ቈላስይስ 1:21-22 NASV)

* ነፃ መውጣት፦ ክርስቶስ በኃጢአት፣ በሞት እና በሰይጣን ኃይሎች ላይ የእኛ ድል ነው።

"የአለቆችንና የባለ ሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።" (ቈላስይስ 2:15 NASV)



3. ክርስቶስ ብቻውን በቂ ነው።

"ማንም ንግግር በማሳመር እንዳያታልላችሁ ይህን እነግራችኋለሁ።" (ቈላስይስ 2:4 NASV)

3.1 በክርክር ተታለሉ፦ እናንተ በእውቀት የበቃችሁ አይደላችሁም ማለት ነው።

"ማንም ንግግር በማሳመር እንዳያታልላችሁ ይህን እነግራችኋለሁ።" (ቈላስይስ 2:4 NASV)

"ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጒዞአችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ። እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን፣ የራሳቸውን ሆድ ነው፤ በለሰለሰ አንደ በታቸውና በሽንገላ፣ የዋሆችን ያታልላሉ።" (ሮሜ 16:17-18 NASV)

3.2 በባህላዊ ምርኮኛ፦ እናንተ ባህላዊ አልሆናችሁም ማለት ነው።

"በክርስቶስ ላይ ሳይሆን፣ በሰዎች ልማድና በዚህ ዓለም መሠረታዊ ሕግጋት ላይ በተመሠረተ ፍልስፍናና ከንቱ ማግባቢያ ማንም ማርኮ እንዳይወስዳችሁ ተጠንቀቁ።" (ቈላስይስ 2:8 NASV)

3.3 በሃይማኖት ይፈረድባችኋል፦ እናንተ ሃይማኖታዊ አይደላችሁም ማለት ነው።

"እንግዲህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ ወር መባቻንና ሰንበትን በማክበር ነገር ማንም አይፍረድባችሁ፤" (ቈላስይስ 2:16 NASV)

3.4 ከመንፈሳዊነት ርቃችኋል፦ በመንፈሳዊ በቂ አይደላችሁም ማለት ነው።

"ዐጒል ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤" (ቈላስይስ 2:18 NASV)

"እነዚህ ሊመጡ ላሉ ነገሮች ጥላ ናቸውና፤ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።" (ቈላስይስ 2:17 NASV)

"እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤ በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ፣ እንደ ተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣ የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ።" (ቈላስይስ 2:6-7 NASV)

ክርስቶስን ብቻ ስበክ!!!




Comments