የእግዚአብሔር ጸጋ መሠረት ነው

የእግዚአብሔር ጸጋ መሠረት ነው::

ቲቶ 2 (አዲሱ መ.ት)

¹¹ ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጦአልና፤
¹² ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛት በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፥ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊ ምኞትን እንድንተው፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል” (ቲቶ 2፡11-12)።

ፀሐይ በምድር ላይ እንደምትወጣ፣ እንደሚታበራ እና እንደሚታሞቅ ፤ ለሰዎች ሁሉ የበራ እና ስለታየው የእግዚአብሔር ጸጋ ክብር ነው ።

የእግዚአብሔር ጸጋ ክብር  የሰው ልጅ በእጁ የያዘው  ፣ በልብም ለሞላው ኃጢአት ለሆነው ጥልቅ ችግራችን መፊትሄ መልስ ነው።

የእግዚአብሔር ጸጋ ክብር  ከኃጢአቻን ሊያድነን እና ሊፈውሰን ይችላል ። በዚህም ለተመረጡት ለካህናት፣ ለባለፀጎች እና ለነገስታት የተፈቀደ ብቻ የተገደበ መዳን ሳይሆን ለሁሉም ሰዎች ለሰው  ልጆች በሙሉ  ጸጋው ይሠራል።

ምሥራቹን ሰምቶ በደስታ የሚቀበል የሰው ልጅ ሁሉ ይድናል! ይህ ሲሆን ህይወትዎ ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ ሁሉም ነገር የተለየ አድስ እና ልዩ ያልተለመደ ይሆናል።

ከእግዚአብሔር ጸጋ ክብር የተነሳ በመጨረሻ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ፊጹም ደስታ እና ሰላም ትወርሳላቹ።

ከእግዚአብሔር ጸጋ ክብር የተነሳ ለወደፊቱ ሕይወታችነ ለነገያችን ተስፋ ሙሉ ተስፋ ሰላም እረፍት ይኖርዎታል።

ከዚያም በመቀጠል ጌታ መንፈስ እንደምፈልግህ፣ እንደሚጠይቅህ እንደምመራህ መኖርን ትለማመዳለህ ፣ ትተገብራለህ።

ከእግዚአብሔር ጸጋ ክብር የተነሳ  ጓደኞችህ፣ ጎረቤቶችህ እና ዘመዶችህ ይህን የምስራች ሰምተው ሕይወታቸውን ለኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሰጡ  ትመሰክራለህ፣ ትፈልጋለህ።

የእርስዎ ለእግዚአብሔር ጸጋ ክብር መታዘዝ የተነሳ ምሳሌ የማወቅ ጉጉታቸውን ቀስቅሶ ለወንጌል ማራኪ ምስክር ሊሆን ይችላል።

ይህ ከሆነ በእግዚአብሔር ጸጋዐሕይወታችን ተቀይሯል።

t.me/yetinsaeqal

JESUS IS RISEN! SUBSCRIBE talewgualu video https://www.youtube.com/watch?v=ANJk-wzRU_Q

Comments