ሁሉ የማንነት እና የአእምሮ ውጤት ነው

ሁሉ የማንነት እና የአእምሮ  ውጤት ነው 
             
 
 የሰውን ክፉ ልብ  ፣የአለምን ክፋት እንዲሁም  ፤ የተሸነፈውን የሰይጣን  የተንኮል ሐሳብ  በቀላሉ  አሸንፈህ በደስታ  በድል በስኬት የምትኖረው በታደሰ ማንነትና  አእምሮህ ነው  

 ያልተፈወሰ ያልታደሰ ማንነትና  አእምሮ  ለምለሙን ምድር፣ ምድረ በዳ ያደርገዋል ፤ የተፈወሰ አእምሮ ግን ምድረ በዳን ያለመልማል
የነገሮች ፣የሰዎች፣ የኑሮ ፣የዘመኑ ፣ ምንነት፣ ግዝፈት  ጨለማነት፣  ክፋት ሳይሆን ህይወትህ የሚወሰነው በማንነትህ እና በአስተሳሰብህ በእይታህ ጤናማነት ነው 

የተለወጠ ማንነት እና አዕምሮ መድሐኒት ሲሰራ ያልተፈወሰው ግን መርዝ ነገራ ነገር ሲቀምም ሲጠነስስ ይኖራል፤ 
 ያልተፈወሰ ማንነት እና አእምሮ የአጋንንት መጫወቻ  ነው ፤ጦርነት ሁሉ ያለው በአእምሮአችን ውስጥ ነው፤ያሸነፈ ማንነት እና አእምሮ ከሌለህ ሁሌም በሽንፈት ትኖራለህ 

የተለወጠ ንግግር ፣ባህርይ፣ ተግባር ሁሉ የተለወጠ ማንነት እና አእምሮ ውጤት ነው 
  የተለወጠ  ማንነት እና አእምሮ የሰላም ፣የእረፍት፣ የደስታ፣ የጤናማ አመለካከት  ሐሳቦች መፍለቂያ  ነው።
 ጤናማ ግኑኝነት  ከእግዚአብሔር፣ ከፍጥረት፣ ከሰዎች፣ 

 ከራስ ጋር የመኖር ምክንያት የተለወጠ ማንነትና አእምሮ ነው 

አእምሮአችንን በእውነት፣በፅድቅ፣በፍቅር፣በቅን በሚያበለጥግ ጤናማ እውቀት እናሰልጥን እናድስ

   ታላቅ #ኢንቪስትመንት የሚጠይቅ  እርሻ ነው አእምሮ

(ማረስ  
መዝራት 
መኮትኮት 
አረም ማስወገድ
 ውሃ ማጠጣት
 ከቀበሮዎች ጠበቅን  ይፈልጋል) 

 ሮሜ6:1-11 
2ቆሮ5:17,
ሮሜ12:2   
ምሳ23:7 
    ማንነት በዳግም መወለድ ፤አእምሮ በእውቀት             ነው አዲስ የተለወጡ የሚሆኑት

    ማንነት እና  ጭንቅላት ውስጥ ነው  ስኬት ያለው  
JESUS IS RISEN! 
 SUBSCRIBE 
 talewgualu video 
 https://www.youtube.com/watch?v=ANJk-wzRU_Q

Comments