Jesusis Risen!
"በሕይወት የመኖርና የመከናወን ሚስጥር..."
ዘዳግም 4 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አሁንም እስራኤል ሆይ፤ በሕይወት እንድትኖሩ፣ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር (ኤሎሂም ያህዌ) ወደሚሰጣችሁ ምድር እንድትገቡና እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ሕግ ስሙ፤ ጠብቋቸውም።
² ባዘዝኋችሁ ላይ አትጨምሩ፤ ከእርሱም አትቀንሱ፤ ነገር ግን የምሰጣችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን (ኤሎሂም ያህዌ) ትእዛዞች ጠብቁ።
በመጀመሪያዎቹ ቁጥሮች እንደምናየው ለእስራኤላውያን #በሕይወት_ለመኖር እና ወደ #ተስፋይቱ_ምድር_ለመግባት የተሰጣቸው #መንገድ አንድ ነው። እርሱም :-
#የእግዚአብሔርን #ሥርዓትና_ሕግ #መስማትና #መጠበቅ!
ያለዚህ መንገድ ከነዓን አይታሰብም! ሌላው ይቅርና ከዮርዳኖስ ማዶ የሚቀሩ ሕዝቦች ከዚህ ብቸኛ #መንገድ ውጪ በሕይወት የሚኖሩበት ሰውኛ ዘዴ ፈጽሞ የለም፤ ቢኖርም መጨረሻው ጥፋት ነው! [ዘኁ 32:20-23]
ምንም እንኳን ወደ ከነዓን መሄጃ መንገዱ #ፍጹምና_አስተማማኝ ቢሆንም ይህን መንገድ ለማሻሻል ወይም ለመቀየር መሞከር ትልቅ ጥፋት ያስከትላል። ስለሆነም መንገዱን ማወቅና መቀበል ብቻም ሳይሆን #ማስተካከያና_እርማት ከመስጠት፣ #ሌላ ቅያስ ከማበጀት መቆጠብም ግድ ይለናል ማለት ነው። የአምላክ መንገድ ቅንና ፍጹም ናትና ቀጥ ብሎ መሄድ ብቻ #ሕይወታቸው ናት!
አስቀድሞ ይኼኛውን መንገድ #የተላለፉት በየጊዜው እንደየጥፋታቸው ተቀጥተዋል፤ #መሪያቸው ሙሴም ቢሆን አላመለጠም። [ዘኁ 20:12]
እውነትም #በጽድቅ ላይ የቆመ፣ #የጸና መንገድ!
እግዚአብሔርን #መከተል ማለት #ትዕዛዙን መከተል ማለት ነው። (ቁ. 3-4)
ከምድረ በዳው እልቂት የተረፉት፣ የተረፉበት ምክንያት ትዕዛዙን በመከተላቸው ነው። የጠፉትም የሕይወትን መንገድ #በመናቃቸው ነው።
ሕጉን መከተል ማለት እግዚአብሔርን መከተል እንደሆነ በሕይወት የተረፉት ሕያው ምስክሮች ሆነው ነበር። (ቁ. 6)
ወዳጆች! ይኼን ሁሉ ማለት ለምን የተፈለገ ይመስላችኋል?.... ከእስራኤል ሕዝብስ ምን እንማራለን?...
የምንኖርባት ዓለም የተበከለች ናት። በኀጢአት ብዛት የሸተተች፤ የከረፋች!
ወደ እግዚአብሔር የሚወስድ ጎርባጣ መንገድ እንኳን የላትም። በጥሻ የተሞላት ነች፤ ዳርቻዋም ገደል ነው! የሞት አፋፍ!
አማኝ ስንሆን ከሌላው የሚለየን የምንኖርበት ዓለም ሳይሆን የምንኖርበት መንገድ ነው (Lifestyle).
ሕይወታችን የሚመራው በሕያው፣ በእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ነው። የጥፋትን መንገድ ከሩቁ ለይተን እምቢ እንድንል ቃሉ ጥበባችንና ብርሃናችን ነው [መዝ. 119:105፣130] ፤
የተስፋ ጮራ የሚፈነጥቅብት፣ ከኀዘን ሸለቆ የምንወጣበት የንስር ከንፍ!
የከበረ ሕይወት የሚቀዳው ከዚህ ቃል ነው።
የእግዜርን መንገድ እግዜሩ ካልነገረን ከማን ልንማር ነው???
የመጨረሻ መልእክት፣
“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤”
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16 (አዲሱ መ.ት)
እግዚአብሔር ለቃሉ ልቦናችንን እንዲከፍት፣ እሺ የሚል ታዛዥ ልብ እንዲሰጠን በግላችን እየለመንነው ዘዳግም 4:1-14 እና ዘዳግም 8 ብናነብ የዚህ ጽሑፍ ሸክም ይበልጥ ይሰማናል።
Comments