አማኝ ስለቤተክርስቲያን ማወቅ ያለበት እውነት
ቤተክርስቲያን የሚለውን ቃል በደንብ ማወቅ አለብን በተለይም ከጥቂት ጊዜ በፊት የመጡት ትውልድ ስለ ቤተክርስቲያን በጥልቀት አያውቁም ምክንያቱም ሲመጡ ትንቢት ፍለጋና ከተለያዩ ችግሮቻቸው ለመላቀቅ ለቁሳቁስ መሟላት ነው ። ያ ስህተት ነው እያልኩ አይደለም ነገር ግን ስለምንሰብብበት ቤተክርስቲያን ሙሉ እውቀት ኖሮን ልንመላለስበት አስፈላጊ ነው ።
በቤተክርስቲያን ውስጥ የምናገለግል አገልጋዮችም ትውልድን ከመውቀስ ቀርበን እውነትንና ትክክለኛ ነገር ማስተማር አለብን ትውልዱን እኛ ከገፋናቸው ከተቸናቸው ቦታ ካልሰጠናቸው ትክክለኛውን አካሔድ ካላሳወቅን ማን መጥቶ ያስተምራል ?
መጸሐፍ ቅዱስ እናንተ የክርስቶስ ቤተመቅደስ ናችሁ ይለናል ይሕ ስለ ግለሰብ ነው የሚናገረው እኔ' አንተ' አንቺ' የመንፈስ ቅዱስ ማደርያዎች ነን ። 1ኛቆሮ 6 እናንተ የክርስቶስ ቤተመቅደስ እንደ ሆናችሁ አታውቁም ? ይላቸዋል
Comments