እውነተኛ መሰረቱ የፀና የፀጋ ህይወት

እውነተኛ መሰረቱ የፀና የፀጋ ህይወት


አማኝ ሊመሰረት እና መስረቱ ሊሆን የሚገባው ኢየሱስ ነው ።  አንዳዶቻችን የተሳለብን አገልጋይ ነው ። ሰው የሚያምነውን ነው ተስፋ የሚያደርገው ፣ ሰው የሚያውቀውን ነው  የሚመስለውን እና ፣ የሚከተለው  ። 

የጳውሎስ ምጥ ሰዎች  ስለክርስቶስ ያውቁ ዘንድ ነበር የሁሉ ነገር ምንጭ የፀጋ ምንጭ የሆነውን ኢየሱስን እናውቅ ዘንድ ነበር ተጋድሎው አብዛኞቻችን ህያው የሆነውን ኢየሱስን ከምናምን ይልቅ የክርስቶስ ቱርፋት የሆነ ነገር ላይ ነው እምነታችን ያለው ።

 እምነታችን ዘይትን እንደምናምን ኢየሱስን ብናምን ብናውቀው ህይወታችን ምን ያህል እግዚአብሔር በሚፈልገው አቅጣጫ በተጓዝነው ነበር ዛሬ የተንተራስናቸው ከኢየሱስ ውጭ የሆኑ ነገሮች ፣ መሰረታችንን ያስጣሉን ከእኛ ላይ ይራገፉ 

እኛ አማኞች ስር ሰደን ፣ ፀንተን ፣ እንደተቀበልነው ልንኖር ልንመላለስ የሚገባው በኢየሱስ ነው ።

አማኝ መሰረቱ ሊመሰረትበት የሚገባው ኢየሱስ ላይ የተቀባው መሲ ላይ ነው ። መሰረታችን ኢየሱስ ሲሆን በምንም ምክንያት ደስታ ከፊቱ ማይጠፋ ፣ ህይወቱ እየለመለመ ያሚሄድ ፣ ፍሬ የማይታጣበት ፣ ሰይጣን እንደፈለገ የማይጫወትበት አማኝ እንሆናለን ።





JESUS IS RISEN! 

Comments