ነብይነት!

ነብይነት!

ነቢይነት እጅግ የተከበረ ቢሆንም በህብረተሰባችን ውስጥ ግን ብዙ ሀሰተኛ እና ጸያፍ ነቢያት አሉ።

እውነተኛ ነቢያት በሰው ወይም ከሰው የሆኑ ሳይሆኑ በኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተክርስቲያን በዓላማ ተሰጡ ናቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ነብይነት በኢየሱስ ክርስቶስ የሚደረግ እንጂ በቤተክርስቲያን ሹመት የምናገኘውና በታዋቂ አገልጋዮች ዘይት ማፍሰስ የምንሆነው አይደለም ማለት ነው፡፡

"እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።" (ኤፌሶን 4፡11-13)

ክርስቶስ ኢየሱስ የትንቢትን ጥበብ የሰጠ እና ሰዎችን በነቢይነት አገልግሎት የሾመ ነው። ማንኛውም እውነተኛ ነቢይ ክርስቶስ ኢየሱስን ለሰዎች የመግለጥ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል።

በአምስቱ የኢየሱስ ክርስቶስ የአገልግሎት ስጦታዎች የተጠራው ሁሉም ሰው አይደለም፡፡ እናንተ ከአምስቱም በየትኛውም ውስጥ አትጠሩ ይሆናል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ምስክር እንድትሆኑ ተጠርታችኋል።

"ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።" (የሐዋርያት ሥራ 1፡8)

አንዳንድ ነቢያት ነን ባዮች ሕዝቡን እንደ ፈለጉት ለማድረግ ስለሚፈልጉ ሕዝቡ በመማር ከእነርሱ ራሱን ነጻ እንዳያወጣ ሕዝቡ መማርን እንደ ስህተት እንዲቆጥር ያደርጋሉ። ማወቅ ያለብን ግን እውነተኛ ነቢያት አስተማሪዎች ጭምር መሆናቸውን ነው።

በእኛ ዘመን በነቢያት እና በአስተማሪዎች መካከል መቀባበል የለም። ወደ አንጾኪያ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ግን በእነርሱ መካከል ያለውን መቀባበል እናገኛለን።

"በአንጾኪያም ባለችው ቤተ ክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፤ እነርሱም በርናባስ፥ ኔጌር የተባለው ስምዖንም፥ የቀሬናው ሉክዮስም፥ የአራተኛው ክፍል ገዥ የሄሮድስም ባለምዋል ምናሔ፥ ሳውልም ነበሩ።" (የሐዋርያት ሥራ 13፥1)

ሀሳቤን ሳጠቃልል ይህን ልል እወዳለሁ፦ አምስቱ የክርስቶስ ስጦታ ከባል ወደ ሚስት ወይም ከሚስት ወደ ባል የሚተላለፍ አይደለም፡፡ አሁን የምናየው ግን ባል ነብይ ከሆነ ሚስትም ነብይ ነች፡፡ ይህ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡

JESUS IS RISEN!
 SUBSCRIBE
 talewgualu video https://www.youtube.com/watch?v=ANJk-wzRU_Q

Comments