በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን የተጠራው የመጀመሪያው ስብሰባ!

በኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን የተጠራው የመጀመሪያው ስብሰባ!



የዚህ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ስብሰባ አጀንዳው በጸጋው ወንጌል ላይ የተቃጣውን የሕጉን ሥርዓት በተመለከተ ነው።

ሀ. ሕግ ወይም ጸጋ

የአይሁድ እምነት ተከታዮች ከአህዛብ ወደ ወንጌል በመጡት ላይ የሙሴን ሕግ ለማስከበር ሞክረዋል፡፡

"አንዳንድ ሰዎችም ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ በሙሴ ሥርዐት መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” በማለት ወንድሞችን ማስተማር ጀመሩ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:1 NASV)

"በክርስቶስ ጸጋ የጠራችሁን እርሱን ትታችሁ፣ ወደ ተለየ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ መዞራችሁ ደንቆኛል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሌላ ወንጌል የለም። የሚያደነጋግሯችሁና የክርስቶስን ወንጌል ለማጣመም ጥረት የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።" (ገላትያ 1:6‭-‬7 NASV)

ጳውሎስና በርናባስ ከክርስቲያናዊ የጸጋ መለኪያ አላፈገፈጉም፡፡ "ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋር ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእምናን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለ ዚሁ ጒዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:2 NASV)

"ለሚያምን ሁሉ ጽድቅ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።" (ሮሜ 10:4 NASV)

"ነገር ግን እኛም ብንሆን ወይም የሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን። ቀደም ብለን እንዳልነው፣ አሁንም ደግሜ እላለሁ፤ ማንም ከተቀበላችሁት ሌላ የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ፣ እርሱ ለዘላለም የተረገመ ይሁን። አሁን እኔ ጐሽ ለመባል የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሰኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሰኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ባልሆንሁ ነበር። ወንድሞች ሆይ፤ የሰበክሁላችሁ ወንጌል ሰው ሠራሽ አለመሆኑን እንድታውቁ እፈልጋለሁ፤ ከማንም ሰው አልተቀበልሁትም፤ ከማንም አልተማርሁትም፤ ይልቁንስ በመገለጥ ከኢየሱስ ክርስቶስ ተቀበልሁት።" (ገላትያ 1:8‭-‬12 NASV)

ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች ወንድሞች ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን በወንጌል ጉዳይ ለመነጋገር ሄዱ፡፡

"ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋር ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእምናን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለ ዚሁ ጒዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ። ቤተ ክርስቲያኒቱም እግረ መንገዳቸውን በፊንቄና በሰማርያ በኩል እንዲያልፉ ላከቻቸው፤ እነርሱም በእነዚህ ቦታዎች ለነበሩት የአሕዛብን መመለስና ማመን ነገሯቸው፤ ወንድሞችም ሁሉ በዚህ እጅግ ደስ አላቸው። ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት እንዲሁም ሽማግሌዎች ተቀበሏቸው፤ የተላኩትም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው። ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው አሉ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:2‭-‬5 NASV)

ለ. ውዝግብ

እስራኤላውያን አምላካቸው ለሰው ፊት የማያዳላ መሆኑን ለመገንዘብ ብዙ ጊዜ ይከብዳቸው ነበር።

ብዙዎቹ ፈሪሳውያን እና እንዲሁም በሐዋርያት ዘመን ወደ ክርስትና የተለወጡ አንዳንድ ሰዎች መዳን ለአይሁዶች ብቻ ነው የሚለውን ሃሳብ አጥብቀው ያዙ። በዚህም ምክንያት ከአሕዛብ ወደ ክርስትና የመጡ ሕዝቦችን መገረዝ እና የሙሴን ሕግ መጠበቅ ይገባችኋል ይሉአቸው ነበር፡፡


"ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው አሉ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:5 NASV)

ለአሕዛብ የወንጌል ዋና መልእክተኞች የሆኑት ጳውሎስና በርናባስ፣ ብዙ አሕዛብ በቅን ልብ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ሲመጡ እና የሕይወት ለውጥ ሲያገኙ አይተዋልና፣ እንዲህ ያለውን ትምህርት ለአፍታ ሊመለከቱት አልቻሉም። በዚያ ያሉ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ጉዳዩን እንዲፈቱ ጥያቄው ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ።

ሐ. የኢየሩሳሌም ጉባኤ

ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በጳውሎስ ላይ በተነሣው ጥያቄ ላይ ለመወያየት ተሰበሰቡ፡፡

"ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ይህንኑ ጒዳይ ለማጤን ተሰበሰቡ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:6 NASV)

ጴጥሮስ ቀደም ሲል በተገለጠው በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ በመመስረት እምነቱን ገልጿል፡፡

"ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜ በፊት በእናንተ መካከል እኔን መርጦ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከእኔ አንደበት ሰምተው እንዲያምኑ ማድረጉን ታውቃላችሁ። ልብን የሚያውቅ አምላክ ለእኛ እንደ ሰጠን ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት የተቀበላቸው መሆኑን መሰከረላቸው፤ ልባቸውንም በእምነት በማንጻት በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? እኛም የዳንነው ልክ እንደ እነርሱ በጌታ በኢየሱስ ጸጋ መሆኑን እናምናለን።” (ሐዋርያት ሥራ 15:7‭-‬11 NASV)

"ጴጥሮስ ይህን እየተናገረ ሳለ፣ ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው። ከጴጥሮስ ጋር የመጡት፣ ከተገረዙት ወገን የሆኑት አማኞች፣ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በአሕዛብም ላይ ደግሞ መፍሰሱን ሲያዩ ተገረሙ፤ ይኸውም በልሳን ሲናገሩና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ስለ ሰሟቸው ነው። በዚያ ጊዜ ጴጥሮስ እንዲህ አለ፤ እነዚህ ሰዎች እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን ስለ ተቀበሉ፣ እንግዲህ በውሃ እንዳይጠመቁ የሚከለክላቸው ማን ነው? ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዛቸው። ከዚህ በኋላ፣ ጴጥሮስ ጥቂት ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲቀመጥ ለመኑት።" (ሐዋርያት ሥራ 10:44‭-‬48 NASV)

ጳውሎስና በርናባስ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ድንቅ ሥራ ገለጹ፡፡

"ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋር ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእምናን ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለ ዚሁ ጒዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ።" (ሐዋርያት ሥራ 15:2 NASV)
ያዕቆብ ሐሳቡን በመጨመር የሸንጎውን አስተያየት ጠቅለል አድርጎ አሳይቷል፡፡

"እነርሱም ተናግረው ሲጨርሱ፣ ያዕቆብ ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፤ ወንድሞች ሆይ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ወገን ለእርሱ የሚሆነውን ሕዝብ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶናል። እንዲህ ተብሎ የተጻፈው የነቢያቱም ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል፤ ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤ ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣ ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም እንዲሹኝ ነው፤ እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’ እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን አሕዛብ እንዳናስጨንቃቸው ይህ የእኔ ብያኔ ነው። ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኵሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤ የሙሴ ሕግማ ከጥንት ጀምሮ በየሰንበቱ በምኵራብ ሲነበብና በየከተማው ሲሰበክ ኖሮአልና።” (ሐዋርያት ሥራ 15:13‭-‬21 NASV)

"በእምነቱ ደካማ የሆነውን ሰው፣ አከራካሪ በሆኑ ጒዳዮች ላይ በአቋሙ ሳትፈርዱበት ተቀበሉት። የአንድ ሰው እምነቱ ማንኛውንም ነገር እንዲበላ ይፈቅድለታል፤ በእምነቱ ያልጠነከረው ሌላው ሰው ግን አትክልት ብቻ ይበላል። ማንኛውንም የሚበላ የማይበላውን አይናቅ፤ የማይበላውም፣ የሚበላውን አይኰንን፤ እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። ሌላውን በሚያገለግል ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? እርሱ ቢወድቅ ወይም ቢቆም ለጌታው ነው፤ ጌታ ሊያቆመው ስለሚችልም ይቆማል። አንድ ሰው አንዱን ቀን ከሌላው የተሻለ ቅዱስ አድርጎ ይቈጥራል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል እንደሆኑ ያስባል። እያንዳንዱ የራሱን ውሳኔ ልብ ብሎ ይወስን። አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው፣ እንዲህ የሚያደርገው ለጌታ ብሎ ነው፤ ሥጋ የሚበላውም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባልና። የማይበላም ለጌታ ሲል አይበላም፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርባል።" (ሮሜ 14:1‭-‬6 NASV)

መ. የድል ጸጋ

ሸንጎው አሕዛብ ክርስቲያኖች ከሙሴ ሕግ ነፃ እንዲሆኑ ወሰነ፡፡
"ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን። ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡22-29)

"ነገር ግን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ በሁሉ ፊት ኬፋን፦ አንተ አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ እንዴት ግድ አልሃቸው? አልሁት። እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ኃጢአተኞችም የሆኑ አሕዛብ አይደለንም፤ ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።" (ገላትያ፡2፡14-16)

ደብዳቤ ተጽፎ ወንድሞች መልእክቱን እንዲያደርሱ ተላኩ፡፡ 

"እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን። ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ። እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፥ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው። አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡23-33)

ሠ. መሪ መንፈስ ቅዱስ

ሐዋርያት እና ሽማግሌዎች፣ በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ፣ ሕጉ በክርስቶስ እንደተፈጸመ እና አሁን በሥራ ላይ እንዳልዋለ ተረዱ።

"ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ … ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡24፤ 27-29)

መገረዝ አያስፈልግም ብለው ወሰኑ። ለጣዖት ከተሠዋ ሥጋ ከመራቅ በቀር ስለ መብላትና ስለ አለመብላት፥ ስለ ቅዱሳን ቀናት፥ ስለ ወር መባቻዎች እና የሰንበት ቀናት ስለመጠበቅ ምንም አልተጠቀሰም።
"እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።" (ቆላስይስ 2፡16-17)

"ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።" (ሮሜ 14፡5-6)

"አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም።" (ሮሜ 7፡6)

በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያለው እውነት፣ የሙሴን ሕግ እንዴት እንደተተካ የሚያሳዩ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው።

ረ. ሁለተኛው የሚስዮናዊነት ጉዞ

ጳውሎስ ከአንጾኪያ ተነስቶ ቀደም ሲል የጎበኟቸውን ከተሞች ለማለፍ ወሰነ፡፡

"ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ። ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር። ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ አለው።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡34-36)

በርናባስ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ይወስድ ዘንድ ወደደና ከእርሱ ጋር ወደ ቆጵሮስ ሄደ፡፡

"በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡37-39)

ጳውሎስ ሲላስን መርጦ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ ሄደ፡፡
"ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።" (የሐዋርያት ሥራ 15፡40-41)


JESUS IS RISEN! 
 SUBSCRIBE 
 talewgualu video 
 https://www.youtube.com/watch?v=ANJk-wzRU_Q

Comments