መንፈስ ብቻ!
1. መንፈስን ማምለክ የሚችለው መንፈስ ብቻ ነው።
"ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።" (ዮሐንስ 4:23-24)
“እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና።” (ፊልጵስዩስ 3:3)
2. መንፈስን ማገልገል የሚችለው መንፈስ ብቻ ነው።
“በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤" (ሮሜ 1:9)
3. የመንፈስን መገለጥ ሊቀበል የሚችለው መንፈስ ብቻ ነው።
“መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው።” (1 ቆሮንቶስ 2:10)
SUBSCRIBE
talewgualu video
https://www.youtube.com/watch?v=ANJk-wzRU_Q
Comments