ቅዱስ ሕዝብ

 ቅዱስ ሕዝብ 

(1ኛ ጴጥ 2)
በዚህ ክፍል ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ ይለናል:: ስለዚህ እኛ ቅዱስ እነደሆንን እንወቅ ቅዱስ ስለሆንን እርኩሰ ነገር ልንነካ አይፈቀድም ምክንያቱም እኛ ቅዱስ ነን ቅዱስ ሕዝብ ማለት የተለየ ማለት ነው ከምን? ከአለም ፣ ከኃጢአት  ከእርኩሰት:ወዘተረፈ  ስለዚህ የእኛ ማንነት በክርስቶስ ኢየሱስ የተቀደሰ ስለሆነ ለእግዚአብሔር ብቻ ልንሆን ተለንተናል 


ቅዱስ ማለት ህይወት የተገባው:የእግዚአብሔር መልክ ያለበትና ህይወት (zoelife) ያለው    ነው  ስለዚህ ቅዱስ የሚለውን አስተሳሰብ በዚህ መንገድ ካልተረዳነው ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ህይወት መኖር አንችልም


እግዚአብሔር አዳምን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር ሲል የእግዚአብሔር መልክ ምን አይነት ነው? የእግዚአብሔር መልክ አንዱ ቅድስና ነው አዳምን ሲፈጥረው በአዳም ውስጥ፥ impart ያደረገው በአዳም ውስጥ፥ Create ያደረገው Nature የቅድስና ማንነት ነው


ቅድስና ከኃጢአት፣ ከሞት፣ ከአለም መለየት ነው ስለዚህ ከቅድስና ውጪ መኖር ስንጀምር ይሄን እናስብ ከኃጢአት ተለይተናል ግን ወደ ኃጢአት እየተመለስን ነው ከአለም ተለይተናል ግን ወደ አለም እየተመለስን ነው  ከሰይጣንና ከሞት ወጥተናል ግን ተመልሰን ወደዚያ እየሄድን ነው


ሌላው ደግሞ ከቅድስና በወጣን ቁጥር ከቅድስና የህይወት standard መመላለስ ባቆምን ቁጥር የእግዚአብሔርን መልክ እያጣን ነው የምንሄደው የእግዚአብሔርን ባህሪ እያጣን ነው የምንሄደው የእግዚአብሔር ባህሪ ውስጥ ያለው ኃጢአት፣ አለም፣ እርኩሰት፣ ሰይጣን ሳይሆን የእግዚአብሔር ቅድስና ነው ያለው ስለዚህ ቅዱስ እንደሆንን እንወቅ በቅድስና እንኑር :: 

Comments