በኢየሱስ ህይወት እና አገልግሎት መማር

በኢየሱስ ህይወት እና አገልግሎት  መማር




ሉቃ 24÷ 9 

#የኢየሱስ_ህይወት በቃል ፣ በድርጊት ፣ በንግግር ፣ በተግባር የተገለጠ ህይወት ነበር ።


ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ ሲመላለስ አገልግሎቱ በታዓምርና በሀይል የተገለጠ ነው ከዚህ በታች ያሉትን እንመልከት


#ኢየሱስ_በዚህ_ምድር_ላይ #በሶስት_ህይወት_ተገልጧል

1. በኑሮ ተገልጧል  2. በእውቀት ተገልጧል  3. በሀይል ተገልጧል  በእነዚህ ተገልጦ ነበር  ያለፈው ብዙዎች ኢየሱስ ጋር መጥተው ከደዌያቸው ይፈወሱ ከአጋንንት ቀንበር ነጻ ይወጡ ነበር 

 #ኢየሱስ_ጋር_ስንመጣ_ተራ_ነገር አናይም ኢየሱስ ጋር ስንመጣ የሚገለጠው እውነት የብዙዎችን አስተሳሰብ ይቀይር ነበር ብዙዎችን ይነካ ነበር 


#ወደእኛ_ስንመጣ_ዛሬም_በዚህ ምድር ላይ ስንመላለስ ልክ ኢየሱስ ተገልጦ ባለፈው አይነት ህይወት ፣ እውቀት ፣ ሀይል ተገልጠን እንድናልፍ ይፈልጋል ።


የእግዚአብሔር መንግስት ንግግር ብቻ አይደለም ጳውሎስ ወንጌላችን በሀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳት እንጂ ቃል ብቻ ወደእናንተ አልመጣሁም ብሎ ይለናል እኛ ውስጥ የገባ ወንጌል  የሚኖር በኑሮ የሚገለጥ ህይወት ነው ።


ወንጌላችን ዛሬ ስናገለግል በዚህ ምድር ላይ ስንመላለስ በጨለማው አለም ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር መሆን አለበት ። 


ወንጌልን በአንድ መልክ አታስቡ አንዳዶቻችን በኑሮአችን በቅድስና ስንኖር ሰዎችን እንማርካለን አንዳንዶችን በእግዚአብሔር እውቀት እንማርካለን ስለዚህ በብዙ አቅጣጫ እንገለጥ ጠቢብ ነን በሚሉ መካከል በእግዚአብሔር ጥበብ እንገለጥባቸው ያኔ ትውልድን ከጨለማው እንናጠቃለን ለዚህ እውነት እንነሳ ።

Comments