ልናደሪገው የሚገባ

1ኛ እውነትን በፍቅር መናገር  እውነትን በፍቅር እየያዝን ( ኤፌ 4÷15)

 ፍቅር ለባልንጀራው ክፋ አያደርግም ፤ስለዚህ   ፍቅር የሕግ ፍፃሜ ነው።( ሮሜ 13÷10)


2ኛ  ሠዎችን ለመቀየር ከመሞከር ይልቅ ስሜታውን መረዳት ።

    ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ፥ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ ።( ሮሜ 12÷15 )


3ኛ ለማነጽ መፈለግ ።

ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ፣ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፋ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ ። (ኤፌ4÷29)


4ኛ ስሜትህን ግለጽ ፣ሃጢያት ግን አትስራ። 

ተቁጡ ኃጢአትንም አታድርጉ።( ኤፌ4÷26)


5ኛ የግል አለመግባባትን በግል መጨረስ ።

ወንድምህም ቢበድልህ ሂደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው።( ማቴ 18÷15 )


6ኛ የሠዎችን ስህተት በመቁጠር አለመያዝ ። 

ፍቅር በደልን አይቁጥርም ( 1ቆሮ13÷5 )


7ኛ ከመናገር በፊት ማሰብ::

 የጻድቅ ልብ መልሱን ያስባል ።( ምሳ 15÷28)


8ኛ ክፋን በክፉ አትመልስ ።

ክፋን በክፋ ፈንታ ( ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።( 1ጴጥ 3÷9 )


9ኛ ባለመስማማት ጊዜ የራስህን የውስጥ ሃሳብ መመርመር ።

በእናንተ ዘንድ ጦርና ጠብ ከወዴት ይመጣሉ ?? በብልቶቻችሁ ውስጥ ከሚዋጉ ከእነዚህ ከምቾቶቻችሁ አይደሉምን ? ( ያዕ 4÷1-2 )


10 ኛ አላስፈላጊ የቃል ምልልስ ማስወገድ። 

የጌታ ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፣ለማስተማርም የሚበቃ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይ ገባውም።( 2ኛ ጢሞ 2÷24 )


11ኛ በማንኛውም ቦታ የግልህን ብቻ ሳይሆን የቡ ድኑንም ፍላጎት መጠበቅ ።

እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት ለባልጀራው ደግሞ እንጂ ።( ፊል 2÷4 )


Hi This_Video_Help You #Subscribe To #Video_Editing_Channel Share For Free Class  #Video_Editing_Class 

https://youtu.be/FUBMa9gDrGM


Comments