ማን ነበር? December 25, 2021 Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps ማን ነበር?እስቲ እኔም ልጠይቅ ካለ ይነገረኝ፣ከአንዱ አምላክ ውጭ አለ ካላችሁኝ፣ጥንት የፈጠርኩትን ህዝብ ያዘጋጀልኝ፣ይነሳና ይጥራ ካለ ይናገረኝ፣ሌላ አምላክ አላውቅም ብቸኛው እኔ ነኝ፣ካለው ከእርሱ ውጭ ዬት ነው ጠይቁልኝ ።እስቲ ጠይቁልኝ ሶስት ነው የምሉትን፣አንዱን ከስንቱ ጋር አባዝተውት ይሆን፣ተሳስተው እንዳይሆን ረስተውት ድምሩን፣አስተካክሉላቸው ንገሩ አንድነቱን፣እስት አሳዪቸው ገልጣችሁ መፅሀፉን፣አጥብቆ እስራኤልን ያስጠነቀቀውን፣አዎ!ያችን ትዕዛዝ የመጀመርያዋን፣እግ/ር አንድ ነው ብላ ምትሰብከውን፣እያዩ እንዳያዩ የታወሩበትን፣ብርሃን ናችሁና አብሩ ያልተረዱትን።ማን ነበር?ንገሩኝ ሰማይን ስፈጥር፣ኤረ እስት ማን ነበር?ስዘረጋ ምድር፣አብሮት የነበረ ከእርሱ ምመካከር፣ይህ ይሻላል ብሎ ሀሳቡን የምሽር፣ዙፋኑን የሚጋራ ዘላለም የሚኖር፣፣ከአንድዬ በቀር ከጎኑ ማን ነበር?ኤረ ማንም የለ እርሱ እንኳን አያውቀው፣ታድያ ዬት አየ ሰው?ልል አምላክ ሶስት ነው።ደግሞ እኮ ይሉናል ወልድ አለ በቀኙ፣መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ተቀምጦአል በጎኑ፣ቆይ እስት ማን ሰጠው ዙፋን ለመሆኑ፣አፋቸውን ሞልተው በአይናቸው እንዳዩ፣ስላሴ አለ ብለው አያፍሩም ስያወሩ።ለነገሩ አያፍሩም ፍርድም አያስፈራቸውም፣ለፍርድ የሚመጣውን ለይተው አያውቁም፣እነርሱ እንዳሰቡት ደግነቱ አይደለም፣ለስላሴም ብሆን ዙፋን ከአንድ ውጭ በሰማያት የለም፣አህዛብ ብናገሩ ብያጉረመርሙም፣የእግ/ርንና የመስሁን ገመድ ከቶ አይበጥሱም፣በእርግጥም እውነት ነው ልለዩአቸው አይችሉም።ብቻ ስለሆነ ነገረ ስራቸው ግራ የመጋባት፣ፍለጋቸው ደግሞ ላም ባልዋለበት፣ቅዱሳን ለማያውቁት ላልሰበኩት ትምህርት፣ከቶ ላልተፃፌ ለስላሴ ተረት፣አሳልፎ ሰጣቸው የአእምሮአቸው ከንቱነት።አቤት!በጣም የገረመኝ እኔን ያስደነቀው፣የአምላክን አንድነት ምክዱ አጥብቀው፣የእየሱስን ወንጌል ያጣጣሉ ንቀው፣ለእኛ ስም ስያወጡልን መናፍቃን ብለው፣ትንሽ እንኳን ለወጉ ማፈር ስገባቸው፣ለማስመሰል እንኳን አለማፈራቸው፣እሱ ያስደንቀኛል በእውነት ድፍረታቸው።በቃ ጠይቁልኝ ሶስት ነው የምሉትን፣ከቻሉ ይመልሱ ታጥቀው ወገባቸውን።የስላሴ ትምህርት ቀድሞ ከዬት ወጣ?እርሱ የማያውቀውን ሰውስ ከዬት አመጣ?ከጎኑ ልያስቀምጥ ዙፋን ላይ ልያወጣ?በዘመን ፍፃሜስ አለምን ልቀጣ፣ከሶስቱ ማን ይሆን ለፍርድ የሚመጣ?ብላችሁ ጠይቁልኝ ለምን አስፈለጌ በራስ ማምጣት ጣጣ፣መቅሰፍትን መጨመር መጥራቱንስ ቁጣ?የድርሻዬን ላውራ ትንሽ ነገር ልበል፣እንፍጠር አንውረድ ማንስ ይሄድልናል፣በአብና በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ልናጠምቅ ታዘናል፣ሶስትነቱን ደግሞ ከዚህ ተረድተናል፣ብለው ለምቃዡ በሉአቸው ያስቀጣል፣መደመር መቀነስ ማሻሻያ ማድረግ የነጠረውን ቃል።እግ/ር ወልድ እግ/ር መንፈስ ቅዱስ አልተባለምና፣ይህ ሁሉ ቅዤት ነው የሰው ፍልስፍና፣አይናችሁን ግለጡ ይከፈት ልቦና፣ከዚያም ወደ መፅሀፉ መለስ በሉና፣ከፍታችሁ አንብቡት ይናገራልና፣እግ/ር አንድ ነው ብሎ ይጀምርና፣ማን ነበር? ከእኔ ጋር ብሎ ይጠይቅና፣ከእኔ በቀር አምላክ የለም ይለንና፣ክብሬንም ለማንም የማልሰጥ ገናና፣ፍተኛው ኋለኛው አልፋና ኦሜጋ፣ብሎ ያረክሰዋል የስላሴን ዋጋ።እናም እላችኋለሁ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ፣መረጃ አይሆንም ቀርቶ ልባል ስሉስ፣ወልድ እኮ ቃሉ ነው መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የራሱ እስትንፋስ፣እስቲ ምኑጋ ነው የሚያስብለው ስሉስ?በሉ ልንገራችሁ ጆሮ ያለው ይስማ፣የሰማውም ደግሞ ላልሰማ ያሰማ፣በእግ/ር አንድነት ሳይታመንማ፣በእየሱስ ስም ጥምቀት ሳይጠመማ፣ሌላ መንገድ የታል ከእርሱ የሚያስማማ፣እናማ! ዕድላችሁ ሳይጎድል ከቅድስቲቱ ከተማ። በሉ ነቃ ነቃ!!ራስን መሸዋወድ ማደንዘዙ ይብቃ፣ዋጋ አላትና ትንሽ ደቅቃ፣የቀደመች መንገድ በፍጥነት ተጠይቃ፣ማምለጥ እኮ ይቻላል ከዚያ የሞት ስቃ።አንተ ጎበዝ ንቃ ሌላ መንገድ የለም ከፍርድ ማምለጫ፣አንድነቱን አምኖ በስሙ መጠመቅ ግዴታ ነውና የሌለበት ምርጫ። Comments
Comments