ለሙታን ሕይወትን መሥጠት

 ለሙታን ሕይወትን መሥጠት 


"ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ.... "ሮሜ 4÷16-17 


መጽሐፍ ቅዱሳችን ከሚነግረን የአምላካችን የእግዚ

አብሔር ባሕሪ ከሆኑት ውስጥ አንዱ ""እግዚአብ

ሔር ለሙታን ሕይወትን ይሰጣል ""የሚለውን ነው

።በሮሜ 4÷17 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ አስደናቂ መረዳቶችን ካስቀመጠባቸው ስፍራዎች መካከል አንደኛው ክፍል ነው።""ለብዙ አህዛብ አባት አደረ

ግሁህ ተብሎ እንደተጻፈ ÷ለሙታን ሕይወትን በ

ሚሰጥ የሌለውን እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነ

በት በአምላክ ፊት የሁላችን አባት ነው።""ይላል ።እ

ዚህ ጋር የሚናገረው አሳብ ስለ አብርሃም ነው።ይ

ህም አባታችን አብርሃም ምን ዓይነት ሕይወት እን

ደነበርው፥ምን ዓይነት እምነት እንደነበረው ፥ምን ዓ

ይነት ተስፋ ይዞ እንዳመነ፥ያብራራል ።መጽሐፍ እን

ደሚናገረው አብርሃም እጅግ ካረጀ በኋላ የመቶ ዓ

መት ሽማግሌ ሆኖ ሳራየዘጠና ዓመት አሮጊት ሆና

ይስሀቅ እንደወለዱ ይናገራል ።ይሄንን ሲያብራራ

ው፦እንደ ሙት የሆነውን የራሱን ሰውነት ሙት መ

ሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተመለከተ ይለዋል ።

አንዳንድ ጊዜ እምነት ሙት ያልሆነውን ነገር ማሰብ

ነው ብለው የሚያስቡ ስዎች አሉ።ነገር ግን እንዲ

ህ ማሰብ ሳይሆን ፥ልክ አብርሃም እንዳደረገውና መጽሐፍ ቅዱስም እንደሚለን ሙት የሆነውን የራ

ሱን ሰውነት ሙት መሆኑን በእምነቱ ሳይደክም ተ

መለከተ፤ያም ማለት እምነቱ ያይ የነበረው አካላዊ

ውን ነገር ሳይሆን ሌላን የእግዚአብሔርን ችሎታና

ብቃት ነው የሚል ነው።ጳውሎስ ያለው አብርሃም ሙት የሆነ ሰውነት፥ሙት የሆነ የሳራ ማህፀንን ሙ

ት መሆኑን እየተመለከተ ነገር ግን ለሙታን ሕይወ

ትን የሚሰጥ አምላክ አለ ብሎ አመነ ማለት ነው።

አሁን ሙት አይደለም አልሞተም እያለ አይደለም ፥

አብርሃም በእምነት ነው የበረታው ! አብርሃም የበ

ረታው በእግዚአብሔር ባሕሪ እና ችሎታ ላይ ነው።

ዛሬም ለእናንተ መንገር የምፈልገው የእግዚአብሔ

ር ባሕሪ በእናንተ ሕይወት ላይ ለሞተ ነገር 

ሕይወትን ይሰጣችኋል  የሚለውን አሳብ  ነው።



  እግዚአብሔር አምላክ በሞት ላይ ሥልጣን  ያለው አምላክ ነው።

Comments