ጤናማ ቃል እና መልካም አደራ

 ጤናማ ቃል  እና መልካም አደራ


ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ 2ኛው ጢሞቴዎስ 1÷14

ላይ በክርስቶስ እየሱስ ባለ እምነትና --ፍቅር ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል ምሳሌ ያዝ መልካሙንም አደራ በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ ጠብቅ ።


ጤናማ ቃል እና መልካም አደራ ይለዋል ።ጤናማ ቃል ጤናማ ህይወትን ይፈጥራል ።ቃል በሰዎችህ ይወት ውስጥ በረከትን እንደሚፈጥር ሁሉ ህይወ ትን እንደሚፈጥር ሁሉ ጳውሎስ ስዎችን ሊጠቅም ወደ ደህንነትም ሊያመጣ የሚችለውን ቃል ሁሉ እንዲናገር ይነግረዋል ።


መልካሙን አደራ ማለትም የተቀበልነውን ወንጌል በንፅህና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንዲጠብቀው ይነግራዋል።ጳውሎስ በግልፅ የጢሞቴዎስ ምሳሌ እና አስተማሪ ነበር ።

ጢሞቴዎስ  ፀንቶ የኖረበትን ጤናማ ህይወት እንዲኖር ምሳሌ ሆኖታል።ዛሬ በቤተክርስቲያን እንዲህ አይነት ስዎች ስላሉ እምነታቸውን ፍቅራቸውን ጤናማ ቃላቸውን ልንከተል ይገባል ።

Comments