የጳውሎስ ስድስቱ ጥያቄዎች ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት

 የጳውሎስ ስድስቱ ጥያቄዎች ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት


"እናንተ የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ! ለመሆኑ ማን መተት አደረገባችሁ? ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ በፊት ለፊታችሁ በግልጥ ተሥሎ ነበር። ከእናንተ ዘንድ አንድ ነገር ብቻ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ መንፈስን የተቀበላችሁት ሕግን በመጠበቅ ነው ወይስ የተሰበከላችሁን በማመን? ይህን ያህል የማታስተውሉ ናችሁን? በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ፍጹም ለመሆን ትጥራላችሁን? በርግጥ ለከንቱ ከሆነ፣ ይህን ያህል መከራ የተቀበላችሁት እንዲያው ነውን? እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁ፣ በእናንተም ዘንድ ታምራትን የሚሠራው ሕግን ስለ ጠበቃችሁ ነው ወይስ የሰማችሁትን ስላመናችሁ?" (ገላትያ 3:1 - 5 NASV)


ጳውሎስ የተጠቀመው ቃል ከበድ ያለ ነው፤ ይህን ቃል በየትኛውም የአዲስ ኪዳን መፃሕፍት ውስጥ አታገኙትም፡፡ 


በትክክል አላሰባችሁም፣ አላስተዋላችሁም፣ ከሃሳባችሁ ውጪ ናችሁ፣ ተታላችኋል፣ አዚም አግኝቷችኋል፡፡ 


በበራላቸው የፀጋ ወንጌል ፀንተው እንዳይኖሩ እንደገናም መሰጠት እንዳይኖራቸው ማስተዋላቸው በሕግ አስተምህሮ ተይዟል፡፡ 


ጳውሎስ ወደ ገላቲያ ሲመጣ ኢየሱስ ክርስቶስን ነበር የሰበከው፤ በስብከቶቹ ኢየሱስን በአግባቡ በፊታቸው በግልፅ ስሎት ነበር፡፡ 


ጥያቄ 1: አዚም ያደረገባቸው የራሳችሁን ጥረት ማከል አለባችሁ የሚል አስተምህሮ ነው፡፡ 


ጥያቄ 2: መንፈስ ቅዱስን የተቀበልነው ከእምነት (ከክርስቶስ) በሆነ መስማት ነው፤ ይህ የሚያሳየው የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት ነው፡፡ 


ጥያቄ 3: የማያስተውሉ ማሰብ ያቆሙ ናቸው፤ እንደ እነዚህ ዓይነት ስዎች የሚሏቸውን ሁሉ የሚቀበሉ ናቸው፡፡ 


ጥያቄ  4: ሰዎች የክርስትናን ሕይወት በጸጋ ጀምረው በራስ ጥረት (በተለያዩ መሥፈርቶች) ፍፁም ለመሆን ይፈልጋሉ፤ ይህ የሚያሳየው ቅድስናን ነው፡፡ 


ጥያቄ 5: እነዚህ ሰዎች በኢየሱስ ከማመናቸው (ኢየሱስን ለመከተል ከወሰኑት ውሳኔ) የተነሣ የደረሰባቸው መከራ ነበር፤ አሁን ግን ያሳለፉትን መከራ ከንቱ የሚያደርግ የሃይማኖት አስተሳሰብ ጥቃት ደርሶበባቸዋል፡፡ 


ጥያቄ  6: ለተአምራት ሌላ መንገድ መፈለግ የለብንም፤ ኢየሱስን በመስማትና በመናገር ተአምራት ይሆናል፡፡ 


ከደኅንነት ይልቅ ትልቅ ተአምራት የለም፡፡ ይህ የሚያሳየን እምነትን (ኢየሱስን) ስንሰማ ተአምራትን መለማመድ ምን ያህል ቀላል እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ 


"በመካከላችሁ ሳለሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ያውም የተሰቀለውን፣ እርሱን ብቻ እንጂ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።" (1 ቆሮንቶስ 2:2 NASV)


የአዲስ ኪዳንን 2/3ኛውን የፃፈው ጳውሎስ የእርሱ አእምሮ በኢየሱስ እና በእርሱ በተፈፀመው ሥራ የተሞላ ነበር፤ እግዚአብሔር የእኛም አእምሮ በኢየሱስ ክርስቶስ እና በእርሱ መስቀል እንዲሞላ ይፈልጋል፡፡


በመስቀል ላይ የተሰቀለውን ኢየሱስን ማየት ማለት በቋሚነት በእርሱ ላይ ትኩረት ማድረግ ማለት ነው፡፡


"ነገር ግን ብሉይ ኪዳን በተነበበ ቊጥር ያ መሸፈኛ እስከ ዛሬ ድረስ ስላልተወገደ ልቡናቸው እንደ ደነዘዘ ነው፤ መሸፈኛው አሁንም አልተወገደም፤ የሚወገደው በክርስቶስ ብቻ ነውና። እስከ ዛሬም ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቊጥር መሸፈኛው ልቡናቸውን ይሸፍናል። ነገር ግን አንድ ሰው ወደ ጌታ ዘወር ሲል መሸፈኛው ይወገዳል።" (2 ቆሮንቶስ 3:14 - 16 NASV)


ጳውሎስ አማኖችን ሲመለከት በመንፈስ  ጀምረው  ወደ መጀመሪያና  አለማዊ ትምህርት  "ሕጉና የሕጉ መርህ"  ዳግም ከተወለዱ በኋላ ሲመለሱ እንዴት የአማኞችን ሃሳብ እንደሚያሳውር ያስገነዝባል፡፡


ኢየሱስ ማን እንደሆነ በተረዳን ቁጥርና የተፈፀመውን (የተጠናቀቀውን) የእርሱን ሥራ ባወቅን ቁጥር አገልግሎት ሁሉ ቀላል እየሆነልን ይሄዳል፡፡

Comments