ወንጌል ስንል ምን ማለታችን ነው? What do we mean by gospel? May 11, 2021 Get link Facebook X Pinterest Email Other Apps ወንጌል ስንል ምን ማለታችን ነው? What do we mean by gospel?ወንጌል ማለት የምሥራች ማለት ነው። በኃጢአት ለተያዘው የሠው ዘር መድሐኒት ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን መነሳቱን የሚያበስር የደስታ ቃል ነው። አንዳንድ መጻፎች ላይ እንዳነበብኩት ወንጌል የሚለው ቃል ከላቲን evangelium / ኢቫንጄሊየም / ከምለው ላይ የተወሰደ ሲሆን፤ ይህም ራሱ ከጥንት የግሪክ ቃል εὐαγγέλιον / ኧውጄሊዮን / አስደሳች መልዕክት ከሚለው የተገኘ ቃል ነው።ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን፣ የዘላለም ሕይወት፣ ትምህርት የሚገኝበት ቅዱስ መልዕክት ነው። ከማቴዎስ እስከ ዮሐንስ ያሉት አራቱ ፀሐፊያን የክርስቶስን ነገር ከልደቱ እስከ ሞቱና እስከ ትንሣኤው ያለውን በሙሉ አንደዘገቡ ይታወቃል። በዚህም የተነሳ ወንጌላውያን የወንጌል ፀሐፊዎች ተብለዋል።ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መፍትሔ አጥቶ ለቆየው ዓለም ሁሉ የኃጢአት በሽታ ብቸኛ መድሐኒት ሆኖ የመጣ የምሥራች እርሱ ነው። መፅሀፍ ቅዱስ እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብከዋለን እንደሚል ከዚህ ውጭ ስለ ወንጌል ለየት ያለ ትርጉምን መልዕክት እንኳን ቢነግሩህ እንዳትሰሙ!!ውድ ወዳጆቼ፤ ለዛሬው የነበረኝ መልዕክት የእስከ አሁኑን ይመስል ነበር። የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ። Comments
Comments