ኢየሱስ ለሰው ዘር በሙሉ ምትክ ሆነ!

ኢየሱስ ለሰው ዘር በሙሉ ምትክ ሆነ! 


እግዚአብሔር በኢየሱስ ላይ ከመቆጣቱ የተነሣ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ተቀጣ! 

የእግዚአብሔር ፍርድ/ቅጣት/ቁጣ በኢየሱስ ላይ ሙሉ በሙሉ ወረደ! ስለዚህ በኢየሱስ ምክንያት የእግዚአብሔር ቅጣት/ቁጣ/በቀል በጭራሽ አይገጥመንም!

ለእኛ ፍርዱ አብቅቷል! አሁን እግዚአብሔር በእኛ ላይ ከመናደድ ይልቅ እርሱ በእኛ ደስ ይለዋል! 

እግዚአብሔር በኢየሱስ ላይ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ተቆጥቶ ነበር! ስለዚህ አሁን እኛ የእግዚአብሔርን ቁጣ በየትኛውም የሕይወታችን አቅጣጫ አንለማመድም!

"የሰማነውን ነገር ማን አመነ?  የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?  በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤ የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እንድንወደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።  በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም። በርግጥ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ፤ ሕመማችንንም ተሸከመ፤ እኛ ግን በእግዚአብሔር እንደ ተመታ፣ እንደ ተቀሠፈ፣ እንደ ተሠቃየም ቈጠርነው። ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በእርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ ጫነው።" (ኢሳይያስ 53:1 - 6 NASV)

እግዚአብሔር በቃሉ ይገሥጻል/ያስተካክላል እንጂ በሕመም፣ በሞት ወይም በማንኛውም ነገር አይቀጣም።

"ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ ሁሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።" (2 ጢሞቴዎስ 3:16 - 17 NASV)

የኃጢአት ቅጣት ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ ላይ መጣ!

የዳዊትና የቤርሳቤህ ልጅ ሞተ። ብሉይ ኪዳን! አዲስ ኪዳን - ቅጣቱ ሁሉ በኢየሱስ ላይ መጣ! አሁን እግዚአብሔር አይቀጣንም!

ከዚህ በፊት ያደረጋችሁት፣ አሁን የምታደርጉት እና ወደፊት የምታደርጉት ሁሉ ቅጣቱ በኢየሱስ ላይ ነው!

ዮሐንስ በመልእክቱ እንደሚናገረው በአብ ዘንድ ጠበቃ ስላለን አሁን እና ወደፊት በምናደርገው ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ቅጣት አይመጣም። ነገር ግን ድርጊታችን በራሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያልሆነ ውጤት አለው።

"ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም።" (1 ዮሐንስ 2:1 - 2 NASV)

ስለዚህ አሁን እግዚአብሔር ይቀጣል የሚል ስብከት፣ ትምህርት፣ ትንቢት፣ ጸሎት እና መዝሙር የሐይማኖት ተራ ወሬ ነው።

Comments