Heavenly Divine Doctor

ሰማያዊው ህኪምና 

                 


ምድራዊ ሀኪሞች በስለት ተጎድቶ የቆሰለን ሰው መልሰው የሚያክሙት በስለት አካሉን በመቁረጥ በመስፋት በመጠገን ነው። ልምድ ያላቸው ሀኪሞች የተጎዳን ሰው ሰውነት በስለት ሲቀዱ፣ የሚወገደውን ቆርጠው ሲጥሉ ዙሪያቸውን ጀማሪ (ልምድ የሌላቸው) ዶክተሮች በተግባር እየተመለከቱ ይማራሉ። በዚህ መንገድ ታማሚው ከህመሙ ሊያገግም ይችላል።


ሰማያዊው ህኪም ክርስቶስ ወደ ምድር በሥጋ ተገልጦ በተመላለሰባቸው ወራቶች የተለያዩ ቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ሽባዎች፣ ጎባጣዎችን፣ ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸውን ዓይነ ስውሮችን ሲያክም ሲፈውስ ዙሪያውን አዳዲስ ተማሪ የሆኑት ደቀመዛሙርቱ ከበው ይመለከቱት ነበር። 


ጌታ ህሙማንን ሲፈውስ እንደዚህ ዓይነት ነገር ከቶ አናይም!! ማደንዘዣ ወግቶ፣ ግሉኮስ ሰክቶ፣ አካልን ወግቶ፣ ሰውነትን ቆርጦ ደም ፈሶ፣ ታማሚው እያለቀሰ እየተሰቃየ ሳይሆን በሚነቅለውና በሚተክለው ቃሉ ህመምተኛውን ሁሉ ይፈውሳል። የሚደንቀው መፈወሱ ብቻ ሳይሆን ከስቃይ ጋር የሚኖረው ህመምተኛው ያለምንም ስቃይ መፈወሱ ነው። 


ዛሬ ከህመም ጋር ዘመናትን ያስቆጠራችሁ፣ ችግራችሁ ለሰሚም ለተመልካችም እንቆቅልሽ የሆነባችሁ፣ ከሀኪም የተሰወረ ፈውስ አልባ የተባለ፣ የሚያድነኝ ከወዴት ይምጣ የምትሉ ሁላችሁ! ያለስቃይ ስቃያችሁን የሚያስወግድ፣ ያለ ስለት ቁስላችሁን የሚጠግን፣ ያለ ትግል ግብግባችሁን የሚያስጥል የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አጥንትና ጅማትን እስኪለይ የሚወጋ ቃሉ፤ ዛሬ ከህመማችሁ ድናችኋል በሚለው የፍቅር ቃሉ ወደ እናንተ ይምጣ፤ እያልኩኝ ለዛሬ የነበረኝን መልክት እዚህ ላይ አበቃለሁ። በጣም እወዳቸዋለሁ፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።                  

Comments