መንፈሳዊ እርጅና
መንፈሳዊ እርጅና፦ መንፈሳዊ ዓለም ውስጥ አካል መሆን ስታቆሙና አባል ብቻ ስትሆኑ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ ከመንፈሳዊ ዓለም ጡረታ መውጣት ማለት ሲሆን ትርጉሙ ማዕረግ ያለው ስልጣን የሌለው ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ የእግዚአብሔርን ቤት መልመድ ማለት ሲሆን ትርጉሙ ለምዳችሁ መለመድ ማለት ነው፡፡ የማይለመዱ ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የማይለምዱ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ በመንፈሳችሁ መመራት ስታቆሙና በስሜታችሁ መመራት ስትጅምሩ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ በእግዚአብሔር ቃል መመራት ስታቆሙና በሰው ቃል መመራት ስትጀምሩ ማለት ነው፡፡ ያረጁ አማኞች ምልክታቸው ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የእግዚአብሔር ሰው የሚናገራቸውን ቃል ይጠብቃሉ፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ መፀለይ ስታቆሙ ማፀለይ ስትጀምሩ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ ከመሽከም ወደ ሸክምነት ስትቀይሩ ማለት ነው፡፡ ትርጉሙ መንፈሳዊ ዕድገት ማቆም ማለት ነው፡፡ ሲብራራ ሳያድጉ ማደግ ማለት ነው፡፡
መንፈሳዊ እርጅና ማለት፦ ለህይወታችሁ ከጌታ ውጪ መንፈሳዊ ምርኩዝ መጠቀም ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊ እርጅና የአዲስ ነገር ጠላት የቀጣይ ደረጃ ግድግዳ ነው፡፡
" ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳን የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል። " (2ኛ ቆሮ 4፥16)
Comments