ከአካላዊ መንፈሳዊ ይበልጣል

 ከአካላዊ መንፈሳዊ ይበልጣል


እኛ በሃይማኖታዊ ቡድን ወይም በትምህርታዊ ዶግማ የተሰበሰብን ሳይሆን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የመቤዠት ሥራ ከማይጠፋ ዘር የተወለድን እና በአንድ መንፈስ በመጠመቅ አንዱን መንፈስ የጠጣን ዘላለማዊ ቤተሰብ ነን። 


"ሁሉ ነገር ለእርሱና በእርሱ የሚኖር እግዚአብሔር፣ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት፣ የድነታቸውን መሥራች በመከራ ፍጹም ሊያደርገው የተገባ ነበር። ሰዎችን የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሰዎች ከአንድ ቤተ ሰብ ናቸው፤ ስለዚህ ኢየሱስ ወንድሞች ብሎ ሊጠራቸው ዐያፍርም፤" (ዕብራውያን 2:10 - 11 NASV)


"ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን ሕያው በሆነና ጸንቶ በሚኖር፣ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከማይጠፋ ዘር ነው። ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል፣ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤" (1 ጴጥሮስ 1:23- 24 NASV)


"አይሁድ ወይም የግሪክ ሰዎች ብንሆን፣ ባሪያ ወይም ነጻ ሰዎች ብንሆን፣ እኛ ሁላችን አንድ አካል እንድንሆን በአንድ መንፈስ ተጠምቀናልና፤ ሁላችንም አንዱን መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል።" (1 ቆሮንቶስ 12:13 NASV)


ቤተክርስቲያን በማህበር ሳይሆን በቤተሰብነት መንፈስ ውስጥ ስትሆንና እንደ አንድ አካል መፍሰስ ስትጀምር የእግዚአብሔር ኃይልና ፍቅር በዓለም ሁሉ (በሰው ዘር በሙሉ) መገለጥ ይጀምራል።


ማንኛውም ነገር ከአካላዊ ዓለም ከተጀመረ ውጤቱ ግራ መጋባት እና ቀውስ ነው። መንፈሳዊውን በትክክል በመረዳት ስንኖር በአካላዊው ላይ ለሚመጣው አሉታዊ ተጽዕኖ መፍትሔ ማበጀት እንችላለን።


ዛሬ ከእጮኛዬ ጋር ስንነጋገርበት የነበረው እውነት

Comments