እግዚአብሔር በምክንያት የለሽ ፍቅር አፍቃሪ ነው!
የእግዚአብሔር ፍቅር በጊዜ የማይወሰን ዘላለማዊ የሆነ ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ከቅድመ ሁኔታም ውጪ ነው፡፡
"እግዚአብሔርም ከሩቅ ተገለጠልኝ እንዲህም አለኝ። በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህ በቸርነት ሳብሁሽ።" (ኤርሚያስ 31:3)
"በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።" (ዮሐንስ 3:16)
እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ቋሚና በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ነው፤ ምክንያቱም እርሱ የወደደን እኛ በሰራነው ሳይሆን ኢየሱስ በመስቀል ላይበሰራው ነውና፡፡
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ፊቱ ወደኛ የሆነና ማንንም ሰው የሚወድ ነው።
"ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንምማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።" (1ኛ ዮሐንስ 4:10)
ወንጌል እግዚአብሔርን በተመለከተ በትክክል ማን እንደሆነ የሚናገር መልካም ዜና ነው፤ ዛሬ በብዙዎች ዘንድ የተለመደው የወንጌል ትርጉም እግዚአብሔር "ቁጡ አምላክ" ነው የሚል ነው፡፡
"የቁጡ አምላክ" ጽንስ ሀሳብ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን መመልከት የማይችል በጣም ቅዱስ አምላክ መሆኑን ይገልጻል፤ ብዙዎች እግዚአብሔር ከሰዎች ዘወር እንደሚል የሚጠቅሱትም የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደዚያ አይሉም፡፡
"ዓይኖችህ ክፉ እንዳያዩ ንጹሐን ናቸው፥ ጠማምነትንም ትመለከት ዘንድ አትችልም፤ አታላዮችንስ ለምን ትመለከታለህ? ኃጢአተኛውስ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሲውጠው ስለ ምን ዝም ትላለህ?" (ዕንባቆም 1:13)
"ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።" (ኢሳይያስ 59:2)
የቁጡ እግዚአብሔር ሰባኪዎች እግዚአብሔር የሚቃወሙትን ሕዝብ ይቀጣል፣ እኛ አስቀድመን ወደ እግዚአብሔር ብንመለስ እርሱ ወደ እኛ ይመለሳል ይላሉ፡፡ አዳም ከእግዚአብሔር ፊቱን ሲመልስ እግዚአብሔር ወደ እርሱ መጣ፤ አብርሃምም ፊቱን ከእርሱ ሲመልስ እግዚአብሔር ወደ እርሱ መጣ፡፡
"እነርሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእግዚአብሔርን የአምላክን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፤ አዳምና ሚስቱም ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ። እግዚአብሔር አምላክም አዳምን ጠርቶ። ወዴት ነህ? አለው። እርሱም አለ። በገነት ድምፅህን ሰማሁ፤ ዕራቁቴንም ስለ ሆንሁ ፈራሁ፥ ተሸሸግሁም።" (ዘፍጥረት 3:8-10)
"አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና። እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤" (ዘፍጥረት 17:1)
የእግዚአብሔር ፊት ሁልጊዜ ወደ እኛ ነው፤ የእኛ ውድቀት፣ ኩነኔና ፍርሃት የእግዚአብሔርን ፍቅር ፈፅሞ አያጠፋውም፤ ምናልባት እኛ እግዚአብሔርን ማየት ባንችል እንኳ እግዚአብሔር ግን እኛን በፍቅር ያየናል።
ፍቅር ከሁሉ የላቀው ሕይወትን የሚሰጥ መስዋዕት ምሳሌ ነው፤ እግዚአብሔርን ለማወቅ ፍቅርን ማወቅ ነው፤ እግዚአብሔርም በአይሁድ ረቢ በኢየሱስ ክርስቶስ ቁስልና ደም በኩል ያለውን ፍቅር አፈሰሰ፡፡
"እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ እኛም ስለወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል።" (1ኛ ዮሐንስ 3:16)
ክርስቶስ ገና ኃጢአተኞች በነበርንበት ጊዜ ስለኛ የመሞቱ እውነት የሚያሳየን እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር የሚያስረዳ ነው፡፡
"ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን። ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤" (ሮሜ 5:8-10)
እውነተኛ ፍቅር የተገለጠው እግዚአብሔር ያለ ማንም አስገዳጅነት በፈቃዱልጁን የኃጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ በመላኩ እንጂ እኛ እርሱንበመውደዳችን አይደለም፡፡
"ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንምማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነውአይደለም።" (1ኛ ዮሐንስ 4:10)
Comments