ቤተክርስቲያን የመክፈት ሱስ ያለባቸው የማይሉት የለም
ከአሁን በፊት የአህያ መንጋጋ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን፣ በጩኸት የተገኘ ምንጭ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እና ፈልቶ የቀዘቀዘ የቃሉ ወተት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የሚል በፌስቡክ ፖስት ተደርጎ ተዋውቀን ነበር። አነሆ አሁን ደግሞ የዳዊት ውንጭፍ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን፣ የያዕቆብ መሰላል ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እና እናንተ ተኙ እኛ እንጸልያለን ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን የሚል ተዋወቁ።
የሳምሶን ቀበሮዎች ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን Coming Soon lol
ክቡር የሆነው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ እውነተኛውን የክብሩን ወንጌል እውቀት ብርሃን ከማጣቱ የተነሣ ሐሰተኛ በሆኑ ሐዋርያት እና ነቢያት አጭበርባሪነት ለዝርፊያ የተጋለጠ መሆኑ የታወቀ ነው። ምንም እንኳ ሕዝቡ ከሰጣቸው እውቅና የተነሣ የእነርሱ ተሟጋችና ደጋፊ ቢሆንም የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ግን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዘነ ስለሆነ በእነዚህ የክርስቶስ አካል በሆነችው ቤተክርስቲያን ላይ ጁንታዎች በሆኑት ላይ ትኩረት ሰጥቶ እርምጃ መውሰድ አለበት እላለሁ።
ማሳሰቢያ፦ ይህ ሲባል ግን እውነተኛ አገልጋዮች የሉም ማለት አይደለም
Comments