ለዓላማ ተጠርታችኋል
ሁሉም አማኝ እግዚአብሔር የወሰነለት ዓላማ በምድር ላይ የሚፈፅመው ስራ አለው። ከመፈጠራችሁ በፊት አስቀድሞ መርጧችኋል መለኮታዊ ተልእኮ አዘጋጅቶላችኋል።
“ ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።” (ወደ ሮሜ ሰዎች 8፥29-30)
ዳግም የተወለዳችሁ እና ፍፃሜ ያላችሁ ልጆች ናችሁ። የተዋጃችሁት ለመክበር ስለሆነ ከፊታችሁ ለውን ያማረና የተዋበ ሕይወት በተስፋ መጠበቅ ትችላላችሁ። አስቡት ያዕቆብ በእግዚአብሔር ለመመረጥ ምን አደረገ! በፍፁም ምንም አላደረገም ሁለቱም ከመወለዳችው በፊት እግዚአብሔር ያዕቆብን ወደድሁ ኤሳውን ግን ጠላሁ ( ሮሜ 9፥13)
መልካም ዜና ያዕቆብ የእግዚአብሔር ምርጫ እንደነበረ እኛም እንደዚሁ ነን የሚል ነው። እኛ ባደረግነው ሳይሆን በመለኮታዊ ምርጫ እና ዕድል ነው። ተጠርታችኋል ከዛ በላይ ለዓላማ፤ እግዚአብሔር ለኤርምያስ ከመፀነሱ በፊት መመረጡን ነገረው።
“ በሆድ ሳልሠራህ አውቅሃለሁ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።” (ኤር 1፥5) አለው! ከመወለዱ በፊት ለድህንነት መለየት ብቻ ሳይሆን ለአህዛብ ነብይ ተደርጎ መቀደሱንና መቀባቱን አያችሁ። በተመሳሳይ መንገድ እያንዳንዱ አማኝ ለዓላማ ተለይቷል፡፡ ራዕይ የምንለው ያንን ዓላማ ነው። የዓላማ ሰዎች ለምን በምድር ላይ እንዳሉ ያውቃሉ።
እንግዲህ ውድ ወዳጆቼ፤ ለዛሬው የነበረኝ መልዕክት የእስከ አሁኑን ይመስል ነበር። በጣም እወዳችኋሉ ለምልሙ፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።
Thank You For Reading subscribe To This Link
https://youtu.be/kfHrJjy8I58
https://youtu.be/eSb5W97C_PY
Comments