ሽልማት ወይስ ስጦታ

 ሽልማት ወይስ ስጦታ


ሽልማት የተሸላሚው የጥረት ውጤት ሲሆን ስጦታ ደግሞ የሰጭውን ለጋሽነት ወይም ወዳጅነት ያሳያል፡፡
ሽልማት ሰርተን የምንቀበለው ነገር ነው። ስጦታ ደግሞ በተቃራኒዊ ሳንለፋ የምናገኘው ነው። ሽልማት የሚገባን ነገር ሲሆን ስጦታ ግን የማይገባን ነገር ነው፡፡

ክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን እንጂ አልተሸለምነውም፡፡ ህይወት እንዲሆነን በስጦታ ተሰጠን እንጂ በሽልማት አልተቀበልነውም፡፡ መጽሐፈ ቅዱሰ የምነግረን እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሸልም ድረስ ሳይሆን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷልና ነው፡፡ ( የዮሐንስ ወንገል 3፡16 ) የሚለን፡፡

ለተወደደ በሙሉ ስጦታ ይሰጥ ይሆናል፤ የተወደደ ሁሉ ግን አይሸለምም፡፡ ኢየሱስ ሽልማት ቢሆን ኖሮ አንዳችንም ባልዳንን ነበር፡፡ ነገር ግን ስጦታ ነውና እንዲሁ ተወደን ተቀበልነው፡፡

ለመዳን ካልሰራን ለመጽደቅ ካልለፋን ግን ደግሞ በፀጋ ድነናል ካልን፤ የራሳችን ጥረት የለበትምና እውነትም የህይወት መንገድ የሆነው ኢየሱስ ስጦታ እንጂ ሽልማት አይደለም፡፡ እንዲሁ በፀጋ የሆነ ነፃ ስጦታ እንጂ እንዲሁ በፀጋ የሆነ ነፃ ሽልማት የለም፡፡ ኢየሱስ ስጦታችን ነው!

Thank You For Reading subscribe To This Link
https://youtu.be/kfHrJjy8I58
https://youtu.be/eSb5W97C_PY

Comments