ከዝሙት ሽሹ
ዝሙት አስጸያፊና የድፍረት ኃጢአት ነው ዲያቢሎስ ራዕይ ያላቸውን ሰዎች ከራዕያቸው የሚያዘገያቸውና ራዕያቸውን ሳያሳኩ እንዲያልፉ ከሚጠቀምባቸው ዋነኛ መሳሪያዎች አንዱ ዝሙት ነው፡፡ ከዝሙት ውጭ የሆኑ ኃጢአቶች ሁሉ የሚሰሩት ከሥጋ ውጭ ነው፤ ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። (1ኛ ቆሮ 6፥18)
“ ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም’’ (1ቆሮ 6:15) ። ከሁሉም ኃጢአቶች ለየት የሚያደርገው የማምለጫው መንገድ መሸሽ ስለሆነ ነው፡፡
ሌቦች ባሉበት እናንተ ላትሰርቁ ትችላላችሁ፣ ዘፋኞች ባሉበት እናንተ ላትዘፍኑ ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ዝሙትን ካልሸሸህ በስተቀር በእንዲህ መልኩ ልታመልጥ አትችልም፡፡ “ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ-መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።” (1ቆሮ 6፥19-20)
መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው። (1ኛ ቆሮ 6፥13)
ሥጋችሁ የእናንተ አይደለም፡፡ የእናንተ ባልሆነ ነገር ላይ ምንም ስልጣን የላችሁም፡፡ የጌታ ስለሆ!! አስታውሱ ሰው የዘራውን ያንኑ በመጨረሻ ቀን ያጭዳል፡፡ በዚህ መንገድ ላይ የላችሁ ንስሐ ግቡ፡፡ ንስሐ መግባት ለየትኛውም ኃጢአት ይቅር ያስብላል፡፡ እንግዲህ ውድ ወዳጆቼ፤ ለዛሬው የነበረኝ መልዕክት የእስከ አሁኑን ይመስል ነበር። በጣም እወዳችኋሉ ለምልሙልኝ፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።
Subscribe And Share for Free Graphics Lovers College Class Certification
#AdobeInDesign
https://youtu.be/o1fHjYHc-Do
#AdobePhotoshop
https://youtu.be/J95RT6J-e5M
#GraphicsCollege
http://skillsharevideoblog.blogspot.com
#SpritualBlog
http://giftchristianblog.blogspot.com
Comments