የተከፈለው የደም ዋጋ

የተከፈለው የደም ዋጋ

የሀጢአታችን ጥልቀት ቢገባን ኖሮ አብዝተን እግዚአብሔርን እንፈልገው ነበር አንዳንድ ጊዜ በህይወታችን ያሉ መልካም እንዲሁም ጥሩ ምግባራትን ተመልክተን ቅዱሳን መድሀኒት የማያስፈልጋቸው እንደሆንን እናስባለን።

እመኑኝ የእግዚአብሔር ቃል ሀጢአተኞች ናችሁ ብቻ አይለንም፤ ሙታን ናችሁ ጭምር እንጂ፣ በደለኞች ናችሁ 

ብቻ አይለንም፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች ጭምር እንጂ።

ወዳጆቼ ልባችን በምን ያህል ጥልቀት ክፉ እና የማይታዘዝ መሆኑን ካላወቅን እግዚአብሔር በህይወታችን ያለውን ቦታ መረዳት አንችልም። እግዚአብሔር ያለ እኛ ይኖራል እኛ ግን ያለ እርሱ ሙታን ነን፡፡ ጥልቅና ጠጣር የሆነው ክፉ ልባችንን ሊቀይርና ሕያው ሊያደርገን ወደሚችል ወደ እግዚአብሔር ምህረት እንሩጥ።

ኢየሱስን ወደ ሕይወታችሁ ጋብዙት ብዬ አልጠይቃችሁም፤ ነገር ግን ባታምኑበት ለዘላለም እንደምትሞቱ በገሀነምም የሚረዳችሁ እንደሌለ ልነግራችሁ እወዳለሁ። መስቀሉ ድራማ አይደለም የብዙዎችን ሀጢአት ለማስተሰረይ የተከፈለ የደም ዋጋ የኢየሱስ የነብሱ ድካም እንጂ። እንግዲህ ውድ ወዳጆቼ፤ ለዛሬው የነበረኝ መልዕክት የእስከ አሁኑን ይመስል ነበር። በጣም እወዳችኋሉ ለምልሙ፤ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር ዘራችሁን፣ ኑሮዋችሁን፣ ቤታችሁን፣ ዘመናችሁንና ትዳራችሁን ሁሉ ይባርክ።                 

Comments