የወንጌል እውነት የጠፋባቸው ሰዎች እንዲህ ናቸው!
ጳውሎስ እና በርናባስ
"በልስጥራንም፣ እግሩ አንካሳ የሆነና ከተወለደ ጀምሮ ፈጽሞ በእግሩ ሄዶ የማያውቅ ሽባ ሰው ተቀምጦ ነበር። ይህም ሰው ጳውሎስ ሲናገር ያደምጥ ነበር። ጳውሎስም ወደ እርሱ ትኵር ብሎ ተመለከተና ለመዳን እምነት እንዳለው ባየ ጊዜ በታላቅ ድምፅ፣ ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም! አለው፤ በዚህ ጊዜ ዘሎ ተነሣና መራመድ ጀመረ። ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ በሊቃኦንያ ቋንቋ፣ አማልክት በሰው ተመስለው ወደ እኛ ወርደዋል! ብለው ጮኹ፤ በርናባስን ድያ አሉት፤ ጳውሎስም ዋና ተናጋሪ ስለ ነበር ሄርሜን አሉት። ከከተማው ወጣ ብሎ የነበረው፣ የድያ ቤተ መቅደስ ካህንም ኰርማዎችንና የአበባ ጒንጒኖችን ወደ ከተማው መግቢያ አምጥቶ፣ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ ሊሠዋላቸው ፈለገ። ሐዋርያቱ በርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል ሮጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ እናንት ሰዎች፤ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እኮ እንደ እናንተው ሰዎች ነን። እናንተም ደግሞ ከዚህ ከንቱ ነገር ርቃችሁ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ ወንጌልን እንሰብክላችኋለን።" (ሐዋርያት ሥራ 14:8 - 15 NASV)
የዚህ ዘመን አብዛኞቹ አገልጋዮች ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው ከነጳውሎስ የተለየ ነው።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ለመስማት የሚከብድ ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነገር እየሰማን ነው። በመሆኑም ይህን ጥያቄ ልጠይቅ እፈልጋለሁ። የዘመኑ የአገልጋዮች እና የአገልግሎታቸው ሁኔታ ምን ይመስላል? መልሱን ለእናንተው ትቼዋለሁ።
Comments