የእግዚአብሔር እውነተኛ ባህሪ መገለጥ ክርስቶስ ብቻ ነው!

 የእግዚአብሔር እውነተኛ ባህሪ መገለጥ ክርስቶስ ብቻ ነው!

አንድ የሃይማኖት ሰው ሲጸልይ እንዲህ አለ "እግዚአብሔር ሆይ ከራሴ እግዚአብሔር አድነኝ"
በብሉይ ኪዳን ኢየሱስ የተደበቀ ነው፤ በአዲስ ኪዳን ግን ኢየሱስ የተገለጠ ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በውስጡ የምናየው አንድ መልዕክት ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ማዕከላዊ ነው ይላል፡፡
“እርሱም። እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው። ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው።” (ሉቃስ 24፡25-27)
”እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤ ነገር ግን ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም።“ (ዮሐንስ 5፡39-40)
ሙሴ፣ ነቢያት እና መዝሙራት በሙሉ እየጻፉ ወይም እያሳዩ የነበሩት ኢየሱስን ነው፡፡
“ፊልጶስም ከእንድርያስና ከጴጥሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበረ። ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ። ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።” (ዮሐንስ 1፡45-46)
ኢየሱስ ለአዲስ ኪዳን አማኝ የመጨረሻው ቃል ነው፡፡
”ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያትተናግሮ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤“ (ዕብራውያን 1፡1-2)
"ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። እግዚአብሔር ብርሃን ነውጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።" (1ኛ ዮሐንስ 1:5)
የክርስትናን እውነት ከሚያምኑት መካከል ስለ እግዚአብሔር ብዙ አመለካከቶች አሉ፤ ሁሉም ሰው የእነሱን አመለካከት ለመደገፍ ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ምዕራፍ እና ጥቅስ ማግኘት እንደሚችሉ ይሰማቸዋል፡፡
እግዚአብሔር በእርግጥ ማን እንደሆነ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
እግዚአብሔርን የማየት መብት ያለው ማን ነው? አዲስ ኪዳን በጣም ትክከክለኛውን መግለጫ ይሰጠናል፤ እግዚአብሔር ልክ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
እግዚአብሔርን በተመለከተ ያለን መረዳትም ፍፁም የሚሆነው በኢየሱስ ነው፤ ሐዋሪያው ጳውሎስ እንደሚናገረው ኢየሱስ የእግዚአብሔር ትክክለኛው አምሳል ነው፡፡
"እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤"(ዕብራውያን 1:3)
በኢየሱስ አማካኝነት የእግዚአብሔር ሙላት በአካል ተገልጦ ይኖራል፤ ኢየሱስን እርሱን ካየነው እግዚአብሔር አብን ተመልክተነዋል፡፡
"በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና።" (ቆላስይስ 2:9)
"ኢየሱስም አለው። አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ። አብን አሳየን ትላለህ?" (ዮሐንስ 14:9)
እግዚአብሔር የሙሴ እና የኢየሱስ ድብልቅ አይደለም፤ እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር አንድ ነው፡፡
አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ፣ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ሰለሞንና ነቢያት ስለእግዚአብሔር የተወሰነ እውቀት ነበራቸው፤ በአባቱ እቅፍ ከነበረው ከአንድያ ልጁ በስተቀር እግዚአብሔርን ማንም አያውቀውም፡፡
"መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድልጁ እርሱ ተረከው።" (ዮሐንስ 1:18)

Comments