"የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም"
የአንዳንድ "ክርስቲያኖች" ሞባይል ወይም ኮምፒውተር ከፍተን ብንመለከተው ብዙ ነገሮች ሊገኙበት ይችላሉ ለምሳሌ ፖርኖግራፊ፣ ወሲብ ቀስቃሽ ፎቶዎች፣ ዘፈኖችና ሌሎች ፍልሞች ልገኙበት ይችላሉ። እንደዚህ አይነት የጨለማ ቁራጮች ከአንድ አማኝ አይጠበቁም።
አንድ ጒደኛዬ መዝሙር ከፍቶልን እያዳመጥን ሳለን ከተወሰኑ ትራኮች በኃላ ዘፈን ብቅ አለ። ምንድን ነው ብዬ ሲጠይቀው "አይ ስለ እናት የተዘፈነ ዘፈን ነው ብታይ እንዴት ጥሩ ዘፈን መሰለህ" አለኝ። የልጁ ክርስትና አጠራጠረኝና ወደ መጽሐፍ ቅዱስ መሄድ ግድ ሆነብኝ!
ገላትያ 5:19
የስጋ ስራም የተገለጠ ነው፥ እርሱም ዘፋኝነት፣ ዝሙት፣ ርኩሰት: መዳራት፣ ጣዖትን ማምለክ፣ ምዋርት፣ ጥል፣ ክርክር፣ ቅንዓት፣ ቁጣ፣ አድመኝነት፣ መለያየት፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ መግደል፣ ስካር፣ .....ይህንም የሚመስል ነው።
አስቀድሜም እንዳልሁ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም።
እንዲሁም 2ጴጥሮስ 2:13 ላይ " በቀን ሲዘፍኑ እንደ ተድላ ይቆጥሩታል፣ ነውረኞችና ርኩሳን ሆነው ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣ ይዘፍናሉ፤ ምንዝር የሞላባቸው ሃጢያትንም የማይተው አይኖች አሉአቸው፤ የማይፀኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፡ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፣ የተረገሙ ናቸው" ይላል።
እንድህ ዘፈን ዘፈን ነው። የሚዘፍኑትም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሆነ ሃጢአት እየሰሩ ነው። ዘፈኑ ስለ እናትም ይሁን ስለ አባት፣ ስለ አጎትም ይሁን ስለ አክስት፣ ስለ ሴትም ይሁን ስለ ወንድ ዘፈን ዘፈን ነው ደግሞም ሃጢአት ነው።
1ተሰሎኒቄ 4:6 ላይ " ....እግዚአብሔር ስለ ሃጢአት ሁሉ የሚበቀል ነውና ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታለል" ይላል።
ስለዚህ የዘፈን አልቤም ያለው ብቻ ሳይሆን የሚዘፍንም ይሁን ዘፈንን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግስት የማይወርስ መሆኑ መታውቅ አለበት።
"ወደ እግዚአብሔር እንመለስ እርሱም ያድነናል"
Comments