እኔና አብ አንድ ነን። "I and the Father are one."

“እኔና አብ አንድ ነን።””

  ዮሐንስ 10፥30

“እኔ እሄዳለሁ ወደ እናንተም እመጣለሁ እንዳልኋችሁ ሰማችሁ። የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”

 ዮሐንስ 14፥28

ኢየሱስ ክርስቶስ እኔና አብ አንድ ነን ሲል በመለኮት በባህሪ በአምላክነት እኩል እንደሆኑ የሚናገር ክፍል ነው።ነገርግን ከኔ አብ ይበልጣል ሲል እኔ ከአብ ጋር እኩል አይደለሁም እያለ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲወርድ በሰው አምሳል በመምጣቱ ከክብሩ ዝቅ ብሎ ደግሞም በሰውነት መገለጡ ለእርሱ አምላክነቱን እንደመቀማት ወይም እደመከልከል ሳይቆጥር መምጣቱን የሚያመለክት ክፍል ነው።የክፍሉ ዋና አንኳር ሀሳብ በሰውነት ከመምጣቱ በፊት ስለ ክብሩ ሳያስብ ማለትም ከዛ ከዙፋን ክብሩ ተነስቶ ራሱን ዝቅ አድርጎ ስለኛ በደል ሲል እና ፍቅሩን በዚህ መንገድ መግለጹን የሚያመለክት ነው እንጅ መበላለጥ የሚያሳይ ክፍል ፈጽሞ አይደለም።

ፊልጵስዩስ 2

⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን።

⁶ #እርሱ_በእግዚአብሔር_መልክ_ሲኖር ሳለ_ከእግዚአብሔር_ጋር_መተካከልን_መቀማት_እንደሚገባ_ነገር_አልቈጠረውም፥

⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥

Comments