ካባው ሳይቀደድ ክርስቶስ አይገለጥም .
❝ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥❞
ሐዋርያት 14: 14
እውነተኛ የክርስቶስ አገልጋዮች ሁልጊዜ የሚያሳዩት ክርስቶስን ነው። እነዛ ሰዎች አማልክት መስሎአቼው ሊሰውላቼው ሲሉ ልብሳቼውን ቀደው ይህን ያደረገው እርሱ ነው ብለው ነው በልባቼው የነበረውን የማይታየውን ክርስቶስን ያሳዩት ።
የአሁኖቹ ደግሞ እንኳን ልብሳቼውን ቀደው እራሳቼውን ሊያዋርዱ ቀርቶ ካባቼውን ደርበው ነው በዛ በከበረ በሚመስል በተዋረደ ካባውስጥ ሆነው አጅሬው ዲያቢሎስ እራሱን የሚገልጥበት
ዲያቢሎስ ምንም ጊዜ እራሱን የሚገልጠው አለም ባከበረቺው እግዝአብሔር በናቀው የተከበረ በሚመስል ባልተከበረ ነገር ላይ ነው ።
ስለዚ በየ ሰገነቱ እና በየ አውደ ምህረቱ የምታከብሮቼው ሰዎች በዲያቢሎስ ተመርጠው የከበሬታ ስፍራ ያላቼው ሰዎች ውስጥ ካባውስጥ ተደብቆ በኢየሱስ ስም እራሱን ይገልጥበታል ።
ሰለዚህ ወዳጄ ጠጋ ብለህ ባለ ካባውን መምህርህን በእግዚአብሔር ቃል እድትመዝነው እመክርሐለው !
Comments