የጠቢብ አይኖች በራሱ ላይ ናቸው ።
The eyes of the wise are in themselves They are on.
ሰው በምድር ላይ ሲኖር ያለውን ሃብት ማ
ወቅ እንዴት መታደል ነው።ሀብቱንም በአ
ግባቡ ማስተዳደር እንዴት ብልህነት ነው።
ሰው ሁሉ በሕይወቱ ውስጥ ልዩ የሆነ እ
ምቅ የሆነ ሀይል አለው።ይህም አቅም እ
ና ሃይል ለግለሰብ የሚጠቅም ብቻ ሳይ
ሆን ዓለምን የሚያስገርም ማንነት ነው።
አንተ ብርቱ ሀያል ሠው ምናልባት ገንዘብ
ሊያጥርህ ይችላል ነገር ግን እውቀት ይ
ኖርሀል ፤ምናልባት እውቀት ሊያጥርህ ይ
ችላል ነገር ግን ጉልበት እና ጤነነት ይኖር
ሃል፤ምናልባት ሃብት ላይኖርህ ይችላል ነ
ገር ግን ጥበብ ይኖርሃል ፤ምናልባት ሃብ
ት አተህ ይሆናል ነገር ግን አንተ በሕይወ
ት አለህ፤ምናልባት ወዳጅ ዘመድ ሃብትህ
ም ሁሉ ካንተ እርቆ ይሆናል ነገር ግን የማ
ይጥል የማይከዳው የሃብት ሁሉ ምንጭ የሆነው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው።
Comments