ይሰማል ወይ?

ድንገት ሳትጸልዩ ከተኛችሁ አጋንንት በመኝታችሁ ላይ ያስቸግራችኋል ተብሎ የተነገራችሁ መልእክት አለኝ።

መልእክቱም ይኼ ነው፦ አለቃቸውና ጀሌዎቹ ተሸንፈዋል።

"ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያቢሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤ እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው።" (ዕብራውያን 2:14 - 15 NASV)

"የአለቆችንና የባለ ሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ።" (ቈላስይስ 2:15 NASV)

በዚህ እውነት መኖር አቁማችሁ እውቅና ከሰጣችኋቸው ችግሩ የእናንተ እንጂ ስላልተሸነፉ አይደለም።

Comments