ክርስትያን ኃጢአትን በስጋ የሚኮንን እንጂ በኃጢአት የምኮነን አይደለም ።(ሮሜ 8፥1-4)

ክርስትያን ኃጢአትን በስጋ የሚኮንን እንጂ በኃጢአት የምኮነን አይደለም ።(ሮሜ 8፥1-4)

ምክንያቱም በስጋ ኃጢያትን የኮነነው ኢየሱስ ክርስቶስ እነርሱ ውስጥ ነውና። ዛሬ ዛሬ ግን የሚታየው በክርስቶስ ነኝ የምል ነገር ግን የክርስቶስን ሕይወት ስለማይኖር በኩኔና በውቀሳ የተሞላ ክርስትያን ነኝ ባዮች ሞልቶዋል። ክርስትያን ግን በክርስቶስ የምኖር ስለሆነ ኩኔነ የለበትም ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ዓለምን ነበረ ይወቅሳቸዋል የተባለው ዛሬ ገን ተገላብጦሽ ሆኖ በክርስቶስ ነኝ የምሉትን ነገር ግን ክርስቶስ በሕይወታቸው ያላወቁትን ና ያልኖሩትን ሁሌ ስለምወቅሳቸው ሁሌ እንዴ አሕዛብ ንሳ ለመግባት ይገደዳሉ እውነተኛ ክርስትያን ግን በክርስቶስ መንፈስ ወደ እውነት ሁሉ የምመራው ነው እንጂ በመንፈስ የምወቀ አይደለም ።

መንፈስ ቅዱስ ለክርስትያን የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆኑ፣በሰማይ ርስት እንዳላቸው፣በክርስቶስ ሆኖ በአብ ቀኝ እንደተሰወሩ፣ከኃጢአት አርነት መውጣታቸውን እየመሰከረ ክርስቶስን በሕይወት ያስተምራል እንጂ አይኮንንም አይወቀስምም... ኃጢያት የምሰራ ሰው ሁላችን እንደምናውቀው በሰው ፍት ብያስመስልም እንኳን አይደለም መንፈስ ቅዱስ ሕልናው እራሱ ይወቅሰዋል ስለዝሕም ይኮነናል ... ለዚህም ነው የሙሴ አገልግሎት የኩነነ የተባለው ሰዎች በአሮጌው ማንነት ሙሴ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ሕግ ለመጠበቅ ተፍ ተፍ ስሉ .. ወድቀው ይገኙና ይወቀሳሉ ፣ ይኮነናሉ።

ክርስትያን ግን ለኃጢአት ስለሞተ አይወቀስም አይኮነንም ስለዚህም ሁሌ ለፀሎት በተንበረከከ ቁጥር ይቅር በለኝ እያሌ አይፀለይም ። ቆይ ክርስትያ ከጨለማ ወደምደነቅ ብርሀን የተጠራ አይደለምን even  ጨለማ ለያሸንፈው የማይችል ብርሀን የበራለት ወይም በውስጡ የተቀመጠለት. ዛሬ ላይ ግን በጨለማ እየተመላለሰን የብርሀን ልጂ ነኝ እያለን በድፍረት እንናገራለን ነገር ግን መጸሐፊ የምለን መንደነው ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት አለን ብለን ማውራት የምንችለው ይህ እውነት ስገለጥልን ብቻ ነው 

1ኛ ዮሐንስ 1

³ እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።

⁴ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን።

⁵ ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።

:- ካልሆነ ግን እራሳች እያሳትን በጨለማ እንመላለሳለን እውነትም በእኛ አይኖርም 

“ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም፤”

1ኛ ዮሐንስ 1፥6

ወገን ንቃ ክርስትያን ሁን !!!!

ጨለማ ና ብርሀን

እግዚአብሔር ና ድያብሎስ

ኃጢአትነ  ና ፅድቅ(ክርስቶስ)

የስጋ ምኞትና(ክፉ) የመንፈስ ፍቃድ

አለም ና እግዚአብሔር

ቅድስና እርኩስ

ሰማያዊና ምድራዊ

የዳብሎስ ልጆችና የእግዚአብሔር ልጆች

ፀጋና ኃጢአት

 በፍፁም የማይገናኙና መቼም የማይታረቁ ነገሮች ናቸው ።

አንድ  ዛፍ ሁለት ፍሬ ልታፈራ እንደማይችል፣ እንድሁም አንድ ምንጭ ሁለት አይነት የምጣፍጥና የሚመረውን እንደማያ ፈልቅ .. እንድሁም ክርስትያን አንድ ፍረ ብቻ  ነው ልያፈራ የምችለው እርሱም የፅድቅ ህይወት(የክርስቶስ ሕይወት)(የመንፈስ ፍረ) ብቻና ብቻ ነው  .....

ቃሉን ለእራሳችን ጠፋት አጣሚመን መፍታትና ማስተማርና እንድሁም ትውልድን ነፃ ልያወጣ ከማይችለው ከደካማ ትምህርት የምንመለሰው መች ይሁን? መጽሐፍ ቅዱስ የምቶረገመው በሕይወት ነው።

Comments